መረጃ‼️
የጅቡቲ መከላከያ ሚንስቴር፣ "አሸባሪ" ባለው ቡድን ላይ ባለፈው ሳምንት የድሮን ጥቃት የፈጸመው በጅቡቲ ውስጥ እንጂ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ እንዳልኾነ ማስተባበሉን የፈረንሳዩ ዜና ወኪል ዘግቧል።
መከላከያ ሚንስቴሩ፣ በድሮን ጥቃቱ ስምንት የቡድኑ አባላት እንደተገደሉ ማስታወቁን ዘገባው ጠቅሷል።
በጥቃቱ ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ሰላማዊ ሰዎች ጭምር እንደተገደሉ የገለጠው ሚንስቴሩ፣ በክስተቱ ዙሪያ ምርመራ መጀመሩን ማስታወቁም ተገልጧል።
የድሮን ጥቃቱ የተፈጸመው፣ ከኢትዮጵያ ድንበር ስድስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ አዶርታ በተባለ አካባቢ ነበር ተብሏል።
የፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌህ አማካሪ፣ የጥቃቱ ዒላማ የጅቡቲ አፋሮች አማጺ ቡድን መኾኑን ማረጋገጣቸውንም የዜና ምንጩ ዘገባ ያመለክታል።
@sheger_press