ፓርቲው የጣሪያ ግድግዳ/የንብረት ግብር መመሪያ እንዲቆም የመሰረተው ክስ በፍርድ ቤቱ ተቀባይነት ማግኘቱን አስታወቀ
እናት ፓርቲ የጣሪያ ግድግዳ/የንብረት ግብር መመሪያ እንዲቆም የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ላይ ሐምሌ 17 ቀን 2015 የመሰረተው ክስ በፍርድ ቤቱ ተቀባይነት ማግኘቱን አስታወቀ።
ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ በአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ አማካይነት ሚያዚያ 3 ቀን 2015 የተላለፈው የንብረት ግብር መመሪያ “ሕግን ባልተከተለ መንገድና የከተማ አስተዳደሩ ባልተሰጠው ስልጣን” የወጣ መመሪያ ነው ሲል መመሪያው እንዲሻር ክስ ማቅረቡን ገልጿል።
ተጠሪ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እናት ፓርቲ ለመሠረተው ክስ 1ኛ ፓርቲው የከስ ምክንያት የለውም፣ 2ኛ የቀረበው ክስ ፓርቲው መብትና ጥቅማቸው አረጋግጠው ያቀረቡት ክስ አይደለም፣ 3ኛ ክሱ በይርጋ የታገደ ነው በማለት ወደ ፍሬ ነገር ክርክር ሳይገባ ውድቅ ተደርጎ መዝገቡ ሊዘጋ ይገባል በማለት ሶስት የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያ በማቅረብ ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱ ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ባስቻለው ችሎት መመሪያ ተፈጻሚነት ሊኖረው አይገባም ተብሎ እንዲሻር በሙሉ ድምጽ ውሳኔ መስጠቱን እናት ፓርቲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
ውሳኔው በተሰጠ የሰዓታት ልዩነት ተጠሪ የከተማ አስተዳደሩ ፋይናንስ ቢሮ በውሳኔው ለሚዲያ መግለጫ እንዳይሰጥ አቤቱታ በማቅረቡ ለ15 ቀን አፈፃፀሙ እንዲሁም ለሚዲያ መግለጫ እንዳይሰጥ የዕግድ ትዕዛዝ ተሰጥቷል ብሏል፡፡
ይሁንና እስከ ዛሬ ጥር 26 ቀን ድረስ ቢሮው ያቀረበዉ ይግባኝ ባለመኖሩና የእግድ ትእዛዙ የጊዜ ገደብም ያበቃ በመሆኑ ፓርቲው የፍርድ አፈፃፀም ስልጣን ላለዉ የአፈፃፀም ፍርድ ቤት ፋይል ለመክፈት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡
የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንትም ለ15 ቀናት የሰጡት የአፈፃፀምና ለሚዲያ መግለጫ እንዳይሰጥ የእግድ ትዕዛዝ ቀነ ገደብ ያበቃ በመሆኑ ይህንን ጋዜጣዊ መግለጫ በዛሬው ዕለት ልንሰጥ ችለናል ብሏል፡፡
እናት ፓርቲ በመግለጫው በቀጣይም "በህዝቡ ላይ ከሕግ አግባብ ውጪ የሚጫኑበትን ሸክሞች ወደ ፍርድ ቤት እያቀረበና በሕግ እየሞገተ የሚያስወግድ መሆኑንና ለዚህም በቁርጠኝነት እንደሚሰራ” ገልጿል ሲል አዲስ ስታንዳርድ ዘገባ ተመልክተናል።
@sheger_press