የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ከሠራተኞች ደመወዝ የፓርቲ አባልነት መዋጮ እንዳይቆርጡ የሚከለክል ረቂቅ ሕግ ተዘጋጀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አዲስ ረቂቅ አዋጅ ለውይይት ያቀረበ ሲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎችን በተመለከተ ካካተታቸው አዳዲስ ጉዳዮች መካከል የፖለቲካ ፓርቲዎችን የገቢ ምንጭ የሚመለከተው ማሻሻያ ይገኝበታል።
በሥራ ላይ ያለውም ሆነ ማሻሻያው በቀዳሚነት የሚጠቅሱት የፖለቲካ ፓርቲዎች የገንዘብ ምንጭ ከአባላት የሚሰበሰብ መዋጮ መሆኑን ነው።
ይህ ዓይነቱ መዋጮ አባላት በፈቃዳቸው ለፖለቲካ ፓርቲው የሚያዋጡት ነው። በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የገዢው ፓርቲ አባል የሆኑ የመንግሥት ሠራተኞች የአባልነት መዋጮ የሚከፍሉት በተቀጠሩበት መሥሪያ ቤት አማካኝነት ከወርሃዊ ደመወዛቸው ላይ ተቀናሽ እየተደረገ ነው።
የገዢው ፓርቲ አባላት የሆኑ የመንግሥት ሠራተኞች በፈቃዳቸው ይህንን መዋጮ የሚያደርጉ ቢሆንም በተለያዩ ጊዜያት የመንግሥት ሠራተኞች ያለፍቃዳቸው ከደመወዛቸው ላይ መዋጮ መቆረጡን በመጥቀስ ቅሬታ የሚያቀርቡባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ።
ምርጫ ቦርድ ያዘጋጀው የማሻሻያ ረቂቅ፤ መሥሪያ ቤቶች ከሠራተኞቻቸው ደመወዝ ላይ የአባልነት መዋጮ የሚቁርጡበትን አሠራር ይከለክላል።
ረቂቁ፤ የመንግሥት ሠራተኛ ከሆነ የፖለቲካ ፓርቲ አባል የሚሰበሰብ የአባልነት መዋጮን "መሥሪያ ቤቱ በቀጥታ ከሠራተኛው ደሞዝ በመቁረጥ አባል ወደ ሆነበት የፖለቲካ ፓርቲ የባንክ ሂሳብ ማስገባት አይችልም" ሲል ክልከላ አስቀምጧል።
ረቂቁ፤ በገቢ ምንጭ ላይ የጣለው ክልከላ ይህ ብቻ አይደለም። የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩዎች "ከማናቸውም ሰው የሚሰጥን ስጦታ ወይም እርዳታን" በግላቸው እንዳይቀበሉ ከልክሏል። በረቂቁ መሠረት ይህንን ዓይነቱን ስጦታ ወይም እርዳታ መቀበል የሚችሉት "በፓርቲው በኩል" ነው።
በዚህ ዓይነት መልኩ እርዳታ የተቀበለ ዕጩ "ድርጊቱ በተፈጸመ ወይም መፈጸሙን ባወቀ በ48 ሰዓት ውስጥ" ለምርጫ ቦርዱ ማሳወቅ እና "በዕጩነት ላቀረበው ፓርቲ የተደረገውን ስጦታ ወይም እርዳታ ማስረከብ" እንዳለበት ረቂቁ ላይ ተቀምጧል።
#BBC
@sheger_press