ጀነራል ታደሰ ወረደ፤ ከመንግሥትም ጋር ይሁን ከሌላ ወገን ጋር ወደ ግጭት የሚያስገባ ነገር እንደሌለ ገለጹ
"ወታደራዊ ሃይልን ወደ ስልጣን የማምጣት ጉዳይ አይታሰብም"
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ፤ ከፌደራል መንግስትም ጋር ይሁን ከሌላ አካል ጋር ወደ ግጭት የሚያስገባ ነገር እንደሌለ አስታወቁ፡፡
“በምንም መልኩ በውስጣችን የሚፈጠር ግጭትና ጦርነት አይኖርም፣ የውስጥ ግጭት ይፈጠራል የሚለው ጉዳይ ዝግ ነው” ያሉት ጄነራሉ፤ “ግጭቱና ጦርነቱ በውስጣችን ይሆናል ወይም ደግሞ ከውጭ በሚኖር ግፊት ይጀመራል የሚለው ጉዳይ ሊያሳስብ አይገባም፣ አይኖርም” ብለዋል።
ባለፉት ቀናት በክልሉ የተካሄዱት ሁነቶች በምንም መልኩ ከወታደራዊ ድርጊት ጋር የሚያያዙ አይደለም ያሉት ጄነራል ታደሰ፤ “በምንም መልኩ ወታደራዊ ሃይልን ወደ ስልጣን የማምጣት ጉዳይ አይደለም፤ ይህ ፈጽሞ የማይሆን ነገር ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት የሀይማኖት አባቶችን ጨምሮ በተለያዩ አካላት የተለያዩ ጥረቶች ቢደረጉም ሊሳካ አልቻለም፤ ችግሩ ከአደራዳሪዎቹ ሳይሆን ከተዳራዳሪ አካላት የመነጨ ነበር ያሉት ጄነራሉ፤ ዋና ተግዳሮት የሆነው “አለመቀበልና እንቅፋት መፍጠር፣ አንዱ ወገን አንዱን ወገን አሸንፎ ለመውጣት ፍላጎት መኖሩ” እንደነበር አስረድተዋል፡፡
ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ታደሰ ይህን ይበሉ እንጂ፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ በሰጡት መግለጫ፤ ህገወጥ ያሉት የህወሓት ቡድን አመራሮች ሥልጣን በሃይል ለመንጠቅ እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴ ወደ ጦርነትና ግጭት እንደሚያመራ ማስጠንቀቃቸው ይታወቃል፡፡(አዲስ አድማስ)
@sheger_press