የፋኖ ሀይሎች በሚፈልጓቸው የአውሮፓ ሀገሮችና አደራዳሪዎች አማካይነት ድርድር እንዲደረግ መንግሥት ‘ፈቃደኛ’ ነው ተባለ‼️
በ #አማራ ክልል የሚንቀሳቀሱት የፋኖ ሀይሎች በሚፈልጓቸው የአውሮፓ አገሮችና አደራዳሪዎች አማካይነት ድርድሮች እንዲደረጉ መንግሥት ‘ፈቃደኛ’ መሆኑን የአማራ ክልል የሠላም ምክር ቤት አስታወቀ።
የምክር ቤቱ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ያየህይራድ በለጠ፣ ምክር ቤቱ ሁለት ዓመቱን ሊደፍን የተቃረበውን የአማራ ክልል ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሁለቱም አካላት ወደ ድርድርና ውይይት እንዲመጡ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል።
በዚህም በሁለቱም አካላት በኩል ለውይይትና ለድርድር “ፈቃደኛነት መታየቱን” ገልጸው "የፌደራል መንግሥት በየጊዜው ለሠላምና ለድርድር ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ዝግጁነቱን በተደጋጋሚ ገልጧል፤ በፋኖ ወገኖቻችን በኩልም በምናደርገው ግንኙንት ድርድርና ውይይት እንደማይጠሉ ነግረውናል" ብለዋል።
አንደኛው ሌላኛውን ያለማመን አዝማሚያ ለውይይት የሚደረገውን ጥረት አስቸጋሪ እንዳደረገው ጠቅሰው አለመተማመኑን ለማስወገድ የፋኖ ሀይሎች በሚፈልጓቸው የአውሮፓ አገሮችና አደራዳሪዎች አማካይነት ድርድሮች እንዲደረጉ መንግሥት ‘ፈቃደኝነት’ ማሳየቱን ጠቁመዋል።
ይህን አስመልክቶ ከአብዛኛዎቹ የፋኖ ሀይሎች ጋር “ውይይቶችን እንዳደረጉ” የገለፁት አቶ ያየህይራድ፣ ከፋኖ አመራሮች ምላሽ በመጠበቅ ላይ መሆናቸውን አመልክተዋል።
የአማራ ክልል የሠላም ምክር ቤት በክልሉ በሚንቀሳቀሱት የፋኖ ሀይሎዎች እና በመንግሥት መካከል እየተካሄደ የሚገኘውን ጦርነት በውይይት እና በድርድር ለመቋጨት የአመቻችነት ሚናውን እንዲወጣ ሰኔ 18 ቀን 2016 ዓ.ም መመስረቱ የሚታወስ ነው።
@sheger_press