#ራያ‼️
ከአላማጣ እና አካባቢው 29 ሺህ ህዝብ መፈናቀሉ ተገለጸ‼️
ተፈናቃዮቹ በቆቦ፣ወልዲያ እና ሰቆጣ ከተሞች መጠለላቸው ተገልጿል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት 29 ሺህ ዜጎች ከራያ እና አላማጣ አካባቢዎች መፈናቀላቸውን አስታውቋል፡፡
እንደ ድርጅቱ ሪፖርት ከሆነ ከሰሞኑ በትግራይ እና አማራ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ባገረሸው ግጭት ምክንያት ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል ብሏል፡፡
ተፈናቃዮቹ በቆቦ፣ወልዲያ እና ሰቆጣ ከተማ በሚገኙ መጠለያዎች ላይ እንደተጠለሉም ድርጅቱ አስታውቋል፡፡
በአካባቢው ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ተጨማሪ ዜጎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ የገለጸው ድርጅቱ ለተፈናቃዮች ውሃ፣ ምግብ እና ሌሎች ህይወት ማቆያ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑንም ገልጿል፡፡
አሁን ላይ ከለጋሽ ተቋማት እና ሀገራት የሚገኘው ድጋፍ እየተሟጠጠ በመሆኑ በአካባቢው ያለው ማህበረሰብ የሚችለውን ድጋፍ እያደረገ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ለተፈናቃዮቹ መጠለያ፣ የሕክምና አገልግሎት እና ሌሎች መሰረታዊ ድጋፎችን ማድረግ ይገባል ያለው ድርጅቱ የኢትዮጵያ አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚሽን ሰራተኞች ወደ ስፍራው ተሰማርተዋልም ተብሏል፡፡
ተፈናቃዮቹ ከአንድ ሳምንት በፊት በሚኖሩባቸው አካባቢዎች የህወሃት ታጣቂዎች ወደ ራያ እና አላማጣ አካባቢዎች መምጣታቸውን ተከትሎ ቤታቸውን ጥለው ለመሰደድ እንደተገደዱ ተገልጿል፡፡
ከተፈናቀሉት 29 ሺህ ዜጎች ውስጥ 70 በመቶዎቹ ህጻናት እና ሴቶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ አዛውንቶች እና ታዳጊዎች ናቸው ተብሏል፡፡
@Showapress