❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #የካቲት ፲፩ (11) ቀን።
❤ እንኳን #ለተጋዳይ_ለታላቁ አባት በቀንና በሌሊት ሰባት መቶ ጊዜ አቡነ ዘበሰማያትን ከስግደት ጋር እየጸለ ለአርባ ዓመት በገዳም ለኖረውና በኋላም ወደ በረሃ ከአንዲት ታናሽ ዋሻ ውስጥም ገብቶ እየተጋደለ ብቻውን ለኃምሳ ዓመት ለኖረ፤ ሁለት አንበሶች እንደሰው ለሚላኩለት #ለባለ_አንበሳው_ለአባ_አውሎግ ለዕረፍት በዓል፣ ለሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ለከበረ ለአባት #ለአባ_በላትያኖስ በንጉሥ ዳኬዎስ እጅ ለአንድ ዓመት ያህል ተሰቃይቶ ኋላም አንገቱን በመሰየፍ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና #ለአባ_ስልዋኖስ ረድእ #ለአባ_በትራ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከኤጲስቆጶስ #ከአባ_አብርሃም_ከመነኰስ_ከአባ_መቃቢስና #ከኮንቲ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከት ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ባለ_አንበሳው_አባ_አውሎግ፦ የዚህ ቅዱስ ወላጆች ፍጹም በወርቅና በብርም የበለጸጉ ናቸው። በአንዲትም ዕለት "አውሎግ ያለህን ገንዘብህን ሁሉ ሽጠህ ለድኆች ሰጥተህ መከራ መስቀሉን ተሸክመህ ና ተከተለኝ" የሚለውን የከበረ የወንጌልን ቃል አሰበና ወዲያውኑ ገንዘቡን ሁሉ ለድኆችና ለችግረኞች በትኖ ወደ አባ አውሎጊን ሔደ እርሱም በደስታ ተቀበለው። ስለ እርሱ እንዲህ የሚለውን ራእይ አይቶ ነበር "እነሆ ወዳንተ ጐልማሳ ይመጣል ተቀበለውና ከሚያገለግሉ መነኰሳት ጋር ቀላቅለው"። እየፈተነውም ሦስት ዓመት ያህል ኖረ ፍጹም የሆነ ቅድስናውንም በአየ ጊዜ የምንኵስናን ልብስ የመላእክትንም አስኬማ አለበሰው። ከሰንበትም እስከ ሰንበት እየጾመ በብዙ ተጋድሎ ኖረ ምግቡም እንጀራና ጨው ነበረ በቀንና በሌሊትም ሰባት መቶ ጊዜ አቡነ ዘበሰማያትን ስግደት ጋር ይጸልያል በዚህም ተጋድሎ አርባ ዓመት ኖረ።
❤ ከዚያም በኋላ ያሰናብተው ዘንድ መምህሩ አባ አውሎጊንን ማለደውና ወደ በረሀ ሔደ ከአንዲት ታናሽ ዋሻ ውስጥም ገብቶ እየተጋደለ ኃምሳ ዓመት ኖረ። ለፍላጎቱም የሚያገለግሉት ሁለት አንበሶችን እግዚአብሔር ሰጠው በአንዲትም ዕለት ታመመ አንሶቹንም "እጠጣ ዘንድ የሞቀ ውኃ እሻለሁ" አላቸው። አንዱ አንበሳም ወደ ተራራ ሒዶ እረኛ አግኝት ወደ አባ አውሎግ አመጣው በአየውም ጊዜ ሰገደለትና "አባቴ ሆይ ምን ትሻለህ" አለው እርሱም "የሞቀ ውኃ ታጠጣኝ ዘንድ እሻለሁ" አለው እንዳለውም አደረገለት ከዚህም በኋላ አንበሳው እረኛውን ወደ ቦታው መለሰው። ያም እረኛ "ለእግሩ ተረከዝ ዓለሙ ሁሉ መጠኑ የማይሆን ጻድቅ ሰው አገኘሁ" ብሎ ለሰው ሁሉ ተናገረ በሰሙ ጊዜም ሰዎች ሁሉ ወደርሱ ተሰበሰቡ፡ በሽተኞችንም ሁሉ አመጡለትና ፈወሳቸው።
❤ በዚያም ወራትም መምህሩ አባ አውሎጊን ጣዖትን የሚያመልኩ የፋርስ ሰዎችን ወደ ቀናች ሃይማኖት ለመመለስ ወደ ፋርስ አገር ሊሔድ ፈለገ ዳግመኛም ልጁ አውሎግን ከእርሱ ጋር ሊወስደው ወደርሱ መልክተኛ ሊልክ ሽቶ ሳለ መንፈስ ቅዱስ አንበሳውን አስገነዘበውና አጽፉንና ወንጌሉን አንሥቶ ተሸከመ። አባ አውሎግንም ጒዞን አመለከተው ተነሥቶም አንበሳውን ተከትሎ ወደ መምህር አውሎጊን ደረሰ እርሱም በደስታ ተቀበለው። ሲጓዝም ከጤግሮስ ወንዝ ደረሱ ውኃውም ተከፍሎላቸው ተሻገሩ ወደ አገሩም ውስጥ በደረሱ ጊዜ አስተማሩአቸው ወደ ቀናች ሃይማኖትም መለሷቸውና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው።
❤ በአንዲትም ዕለት ደግሞ ቅዱሳን በተራቡ ጊዜ ምግባቸውን ይፈልጉላቸው ዘንድ አባ አውሎግ አንበሶችን አዘዘ ሒደውም እንጀራ በአህያ ላይ ጭኖ የሚጓዝ ሽማግሌ አገኙ ሕፃንም ከእንጀራው ጋር አለ። አህያውንም ወደ ቅዱሳን አመጡት ከድንጋጤም የተነሳ ብላቴናው ሞተ ቅዱሳንም ጸልየው ሕፃኑ ድኖ ተነሣ ቅዱሳንም ተመገቡ አንቦሶችም አህያውን ከእንጀራውና ከሕፃኑ ጋር ወደ ሽማግሌው መለሱት።
❤ ከዚህም በኋላ አባ አውሎግ ወደ በዓቱ ተመለሰና ጥቂት ታሞ የካቲት11 በሰላም ዐረፈ። በታላቅ ክብርም ተቀበረ እነዚያ አንበሶችም መቃብሩን እየጠበቁ ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖሩ ከዚያም በኋላ ወደ ዱር ገቡ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ አውሎግ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_በላትያኖስ፦ ይህም ቅዱስ ብልህና አዋቂ የሆነ ታላቅ ተጋድሎን የሚጋደል ነው በሮሜ አገርም ሊቀ ጵጵስና ተሹሞ በቅዱስ ጴጥሮስ ወንበር ላይ ዐሥራ ሁለት ዓመት በሰላም ኖረ ሕዝቡን የቀናች ሃይማኖትን እያስተማራቸው ሳለ መኰንኑ ፊልጶስ በንጉሥ ቀላውዴዎስ ላይ ተነስቶ በገደለው ጊዜ በርሱ ፈንታ ነገሠ በምእመናን ላይ ታላቅ መከራን አመጣ በዚህ በንጉሥ በዳኬዎስ እጅ ብዙዎች በሰማዕትነት ሞቱ። በዘመኑም ሰባቱ ደቂቅ ከእርሱ ሸሹ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዓመት ተኝተው ነቁ እርሱም በኤፌሶን ከተማ መስጊድ ሠርቶ በውስጡ ጣዖታትን አኖረ ሰዎችን ሁሉ ለጣዖታት እንዲሠዉ አስገደዳቸው ለጣዖታት ያልሠዉትንም ገደላቸው።
❤ ይህ የከበረ በላትያኖስም የጣዖታት አምልኮን እንደሚቃወም ሕዝቡም በክብር ባለቤት በክርስቶስ ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ እንደሚያስተምር ንጉሥ በሰማ ጊዜ ወደ ሮሜ አገር ልኮ ወደ ኤፊሶን ከተማ አስመጣውና ለጣዖታት እንዲሠዋ ለመነው። እርሱም ግን ቃሉን አልሰማም ተሣለቀበት አማልክቶቹንም ረገመ እንጂ ንጉሥም ተቆጣ አንዲት ዓመት ያህልም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ የካቲት11 ቀን በሰይፍ ራሱን ቆረጠው የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ በላትያኖስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን።
+ + +
❤ የአባ ስልዋኖስ ረድእ አባ በትራ፦ ይህም ቅዱስ በደብረ ሲና ካለች በዓቱ በነበረ ጊዜ ትርኅምትን ይጠብቅ ነበር በራትም ጊዜ ለሥጋው የሚያሻውን ይመገባል። ፈርኑ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶስ በአደረጉት ጊዜ ትርኅምትን በማብዛት ሰውነቱን እጅግ አደከመ ደቀ መዛሙርቱ "አባታችን ሆይ በገዳም በበአትህ በነበርክ ጊዜ ትርኅምትን እንዲህ አላበዛህም ነበር" አሉት ይህም አባት እንዲህ አላቸው "ያን ጊዜ በገዳም በችግር ውስጥ ነበርኩ ዛሬ ግን ከብዙዎች መካከል በአንድነት አለሁ የምሻውም ሁሉ ብዙ አለኝ ነገር ግን ሥጋዬን ቀጥቼ ብገዛው ይሻላል" እንዲህም እየተጋደለ ኖረ ከዚህም በኋላ የካቲት10 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ በትራ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት 11 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለበትራ_ረድአ_ስልዋኖስ_ወምእኑ። ኤጲስቆጶሰ ዘኮነ በሀገረ ፈርኑ። ከመ እንግር ጽድቆ ወኂሩቶ እዜኑ። ለአፉየ ወልሳንየ በመጠኑ። ዘይረድአኒ መንፈሰ ይፈኑ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የካቲት_11።