❤ በአንዲት ዕለት የሶርያው ንጉሥ ሚስት ቅዱስ አውሳብዮስን አይታው እጅግ ወደደችው፡፡ ከባሮቿም ውስጥ ሁለቱን ልካ ካስመጣችው በኋላ በወርቅ አጊጣ በሐር በተነጠፈ አልጋ ላይ ሆና ጠበቀችው፡፡ከእርሷም ጋር እንዲተኛ ስትጠይቀው "እኔስ ሚስቴንም እንኳን በግብር ያላወኩ ነኝና ተይኝ ንጉሡ ባልሽ በቤት ባይኖር ሰውም ባያየን እግዚአብሔር ግን ያየናልና እንዴት በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት እሠራለሁ? "በማለት ትቷት ሊወጣ ሲል ልብሱን ያዘችው፡፡ እርሱም ሮጦ በማምለጥ ቤተ ክርስቲያን ሲገባ እርሷ ግን በመጮህ ባሮቿ ሲመጡላት" ክፉ ነገርን አድርጎብኝ ሄደ" ብላ በሐሰት ተናገረች፡፡ ጭፍሮቿም ቅዱስ አውሳብዮስን ከቤተ ክርስቲያን አውጥተው እየደበደቡ ወደ ንግሥቲቱ አመጡት፡፡ እጆቹንና እግሮቹንም አሥረው ከከተማ ውጭ በአራት ዕንጨቶች ላይ አሰቀለችው፡፡ ከባሮቿም ውስጥ አንዲቱ በንግሥቲቱ ተልካ ሄዳ አውሳብዮስን "ከተሰቀልክበት እንዲታወርድህ ለእመቤቴ ያለችህን እሺ በላት" አለችው፡፡ እርሱም "የአመንዝራን ቃል አልሰማም" አላት፡፡ ንግሥቲቱም እሺ እንዳላላት ስታውቅ አንገቱን በገመድ አሳንቃ 160 ፍላጻዎችን በሰውነቱ ውስጥ እንዲጭምሩበት አደረገች፡፡ጌታችንም ቅዱስ ሚካኤልንና ቅዱስ ገብርኤልን ልኮለት ፍላጻዎቹን ከሰውነቱ ውስጥ አወጡለትና ፍጹም ጤነኛ ሆነ፡፡ ንጉሡም ከሄደበት ሲመለስ ንግሥት ሚስቱን አውሳብዮስን ለስቅላትና ለሞት ያበቃችው በምን ምክንያት እንደሆነ ሲጠይቃት አንተ በሌለህበት ወደ መኝታ ቤቴ ገብቶ ሊናገሩት የማይገባ ነገር ጠየቀኝ በከለከልኩትም ጊዜ በሥራዩ አሳመመኝ" አለችው፡፡ንጉሡም ተቆጥቶ ቅዱስ አውሳብዮስን ከተሰቀለበት አስወርዶ ካስመጣው በኋላ ለምን ይህን እንዳደረገ ጠየቀው፡፡ አውሳብዮስም እውነቱን በነገረው ጊዜ ጭፍሮቹን ምስክር ይሆኑ ዘንድ ሲጠይቃቸው ንግሥቲቱ ስትጮህ ወደ ውስጥ ሲገቡ ያጋጠማቸውን መሰከሩ፡፡ ንጉሡም የሚስቱን ነገር አምኖ በመቀበል በንዴት የቅዱስ አውሳብዮስን ሰውነቱን በሰይፍ አስቆርጦ ሥጋውን እንደ ላም ሥጋ ቆራርጦ በምንቸት አድርጎ በእሳት እንዲበስል አደረገው፡፡ ነገር ግን አሁንም ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ከምቸቱ አውጥተው ከሞትም አድነው በማስነሣት ፍጹም ጤነኛ አደርገው አቆሙት፡፡
❤ ከሞት ከተነሣም በኋላ በአገሩ ውስጥ ሲሄድ ሰዎች አይተውት ለንጉሡ ስለነገሩት ንጉሡ ድጋሚ ካስመጣው በኋላ አራት ዛንጅሮች በአካላቶቹ ውስጥ በማስገባት እጅና እግሩን አሳስሮ በእሳት ውስጥ ጨመረው፡፡ የከበሩ ሁለቱ ቅዱሳን መላእክት አሁንም መጥተው ፈወሱት፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤልም ነጥቆ ወደ ሰማይ አሳርጎት በዚያው በሰማይ 14ዓመት ኖረ፡፡ ከዚያም ወደ ምድር ተመልሶ መጥቶ ወንጌልን እያስተማረ 40 ዓመት ኖረ፡፡ በእርሱም ትምህርት 85ሺህ አረማውያን አምነው ተጠምቀዋል፡፡ ቅዱስ አውሳብዮስ በመጨረሻ ሰማዕትነቱንና ተጋድሎውን ፈጽሞ የካቲት13 ቀን በክብር ዐርፏል፡፡ጌታችንን፡ኢየሱስም ስሙ ለሚጠራ መታሰቢያውንም ለሚያደርግ እስከ ሰባት ትውልድ ሊምርለት ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አውሳብዮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_ሰርግዮስ፦ የዚህ ቅዱስ አባቱና እናቱ ደጎች ናቸው። የአባቱ ስም ቴዎድሮስ የእናቱም ስም ማርያም ነው። ዕድሜውም ሃያ ዓመት ሲሆነው በክብር ባለቤት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሞት ዘንድ አሰበ ወደ መኰንኑ ቆጵርያኖስም ቀርቦ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ መኰንኑም ጽኑ ሥቃይን ያሠቃዩት ዘንድ ያሥሩትም ዘንድ አዘዘ ጌታችንም ነፍሱን ወደ ሰማይ አምጥቀው የቅዱሳን ሰማዕታትን መኖርያ ያሳዩዋት ዘንድ አዘዘ አይታም ተጽናናች ከሥቃይ ከሕማሙም ፈወሰው።
❤ ቀሲስ አባ መጹንና ሁለት ዲያቆናትም ተጋድሎውን ሰሙ ያን ጊዜም ተነሥተው ወደ አትሪብ አገር ገዥ ቀርበው በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ የጸና ግርፈትም ይገርፋቸው ዘንድ አዘዘ እንዲሁም አደረጉባቸው። ሕዝቡም ሁሉ በዙርያቸው ሁነው ይመለከቷቸው ነበር ስለ ቄሱና ከእርሱ ጋር ስላሉትም አዘኑ ቄሱ ግን ፊቱን ወጀርሳቸው መልሶ ገሠጻቸው አስተማራቸውም "በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ በቀናች ሃይማኖት እንዲህ ጽኑ" አላቸው ከዚህም በኋላ በውኋ ላይ ጸልዮ በላያቸው ረጨ በዚያንም ጊዜ በላያቸው ወርዶአልና የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ተቀበለው በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ራሶቻቸውንም በሰይፍ ቆረጧቸው የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ከዚያም በኋላ ቄሱን ከውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ ይጨምሩት ዘንድ መኰንኑ አዘዘ እግዚአብሔርም ከእሳት አዳነው። ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ ተገለጠለትና እርሱ ስለ ክብር ባለቤት ክርስቶስ ስም ሦስት ጊዜ ምስክር እንደሚሆን አሰረዳው ከእሳት ማንደጃው ውስጥም አወጣው። መኰንኑም ወደ እስክድርያ አገር ላከው ተጋድሎውንና ምስክርነቱን በዚያ ፈጸመ የምስክርኘቱን አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።
❤ ከዚያም በኋላ መኰንኑ ቆጵርያኖስ የከበረ ሰርግዮስን ያቀርቡት ዘንድ አዘዘ ታላቅ ሥቃይንም አሠቃየው የነሐስ መንኰራኵሮችንም አምጥተው ከውስጣቸው አስገብተው አበራዩት ሕዋሳቱም አራት ክፍል ሁኖ ሥጋው ሁሉ ተቆራረጠ ጌታችንም አድኖ ያለ ጉዳት በጤና አስነሣው። ዳግመኛም እንዲሰግድለት ጣዖትን አመጡ ቅዱሱ ግን ሲረግጠው ወድቆ ተቀጥቅጦ ደቀቀ መኰንን ቆጵርያኖስም አይቶ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ "አምላክ ቢሆን ራሱን ማዳን በቻለ ነበር" አለ።
❤ ከዚህም በኋላ የጭፍራ አለቃ ስሙ አውህዮስ የሚባል የከበረ ሰርግዮስን ፈልጎ ያዘው ቆዳውንም ገፈው በተቀላቀለ ኮምጣጤና ጨው ቊስሉን ያሹት ዘንድ አዘዘ ጌታችን ግን በሥቃዮች ላይ ያጸናውና ያበረታው፡ ነበር። እናቱና እኅቱም ሰምተው ወደርሱ መጡ በአዩትም ጊዜ በላዩ አለቀሱ ከኀዘንም ብዛት እኅቱ ነፍሷን አሳለፈች የከበረ ሰርግዮስም ስለ እኅቱ ወደ ጌታችን ጸለየ ከሞትም ድና በሕይወት ተነሣች። ያን ጊዜ የሰማዕታትን ገድል የሚጽፍ የአቅፋስ፡አገር ሰው የከበረ ዮልዮስ መጣ ገድሉንም ሁሉ ከእርሱ ተረዳ ለሥጋውም እንደሚያስብ ቃል ገባለት።
❤ ከዚህም በኋላ ደግሞ የከበረ ሰርግዮስን በመንኰራኵር ውስጥ ያሠቃዮት ዘንድ በጆሮዎቹ የእሳት መብራቶችን እንዲጨምሩ የእጆቹንና የእግሮቹን ጥፍሮች እንዲነቅሉ በአንገቱም ከባድ ደንጊያ አንጠልጥለው ከብረት ዐልጋ ላይ አስተኝተው ከበታቹ እሳትን እንዲያነዱ አውህዮስ አዘዘ እንዳዘዘውም አደረጉበት ጌታችን ኢየሱስ ያጸናውና ያለ ጥፋት በጤና ያስነሣው ነበር። የሠራዊት አለቃ አውህዮስም ማሠቃየቱን በደከመ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ፡አዘዘ የከበረ ሰርግዮስ ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ወደ አባቱና ወደ እናቱ ወደ ወንድሞቹም ላከ ዘመዶቹ ሁሉም የእርሱ የሆኑ ሰዎችም መጡ በአፋም ልጓም ለጒመው ቸብቸቦውን ወደሚቆርጡበት ሲስቡት አገኙትና መኰንኑን የረከሱ ጣዖታቱንም ረገሙ መኰንኑም ከከበረ ሰርግዮስ ጋር ሁሉንም ቸብቸቧቸውን እንዲቆርጡ አዘዘ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ።