⇣【ፆም】⇣
ምንነቱ/ድንጋጌው /ሚስጥሩ
ــــــــــــــــــــــــ❀•▣ ▣•❀ــــــــــــــــــــــــ
❨በቋንቋ ደረጃ❩:- ከአንዳች ነገር ከንግግርም ይሁን ከምግብ መቆጠብ ማለት ነው።
ለዚህም ማስረጃ አሏህ ስለ መርየም ሲተርክልን እንዲህ ይላል፡
قوله تعالى:﴿إِنِّي نَذَرْتُ لِلرَّحْمَنِ صَوْمًا﴾
❝ለአዛኙ አምላኬ ፆምን ተስያለሁ❞
ሱራ አል-መርየም :26
❨ሸሪዐዊ ትርጓሜው❩፡ ከጎህ መቅደድ ጀምሮ ፀሀይ እስክትጠልቅ ድረስ ከማሰብ ❪ከኒያ❫ ጋር ፆምን ከሚያስፈቱ ነገራቶች መቆጠብ የሚለውን ያስይዛል ።
ፆም የተደነገገበት ጊዜ
ـــــــــــــــــــ❀•▣ ▣•❀ـــــــــــــــــــ
የረመዷን ፆም በሁለተኛው አመተ - ሂጅራ በሻእባን ወር ላይ ተደነገገ።ፆም ከኛ በፊት የነበሩ ህዝቦች ዘንድ እንዲሁም በነብዩﷺ ዘመን ይኖሩ የነበሩ አህለል ኪታቦች ዘንድ ይታወቅ ነበር።
አሏህ እንዲህ ይላል:-
قوله تعالى:﴿يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِن
قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ﴾ البقرة: ۱۸۳.
❝እናንተ ያመናቹ ሠዎች ሆይ!..ፆም ለእነዚያ ከእናንተ በፊት ለነበሩት ❨ህዝቦች በግዴታነት❩ እንደተደነገገ ሁሉ በእናንተም ላይ ተደንግጓል..ጥንቅቆች ትሆኑ ዘንድ❞
ሱራ አልበቀራ 183
👉ይህም ማለት ይህ አንቀፅ ከመውረዱ በፊት የረመዳን ፆም ግዴታነት አልተደነገገም ነበር።
⚜የነብዩﷺ ኡመት ከሌሎች ኡመቶች ጋር በፆም ድንጋጌ ላይ ቢጋሩም የረመዳን ፆም ግዴታ በመሆኑ ላይ ግን ከሌሎች ኡመቶች ጋር ይለያያሉ።
የረመዳን ፆም ግዴታ ለመሆኑ ማስረጃ
ــــــــــــــــــــــــــ❀•▣ ▣•❀ــــــــــــــــــــــــ
የረመዳን ፆም ግዴታ መሆኑ ማስረጃው የአሏህ ንግግር ነው፦
قوله تعالى: ﴿شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَى وَالْفُرْقَانِ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ﴾ البقرة: ١٨٥
❝❨አሏህ ትፆሙት ዘንድ የወሰነው❩ የረመዷን ወር ለሰው ዘር መመሪያ የሆነው ❨መለኮታዊ❩ አመራር እና ❨እውነት ከ ሀሠት❩ ለመለየት የሚያስችሉ ግልፅ አናቅፅ የሠፈሩበት ቁርዐን የወረደበት ወር ነው። ከመካከላቹ በዚህ ወር የተገኘ ወሩን በፆም ማሳለፍ አለበት❞
ሱራ አል-በቀራ 185
የአሏህ መልክተኛﷺ እንዲህ ይላሉ፡ ❝እስልምና የተገነባው በአምስት ነገራቶች ነው ሸሀደተይን፣ ሰላትን ደንቡን ጠብቆ መስገድ፣ ዘካን መስጠት፣ ሀጅ ና ረመዳንን መፆም ናቸው ❞።
📜 ቡኻሪና ሙስሊም ሌሎችም ዘግበውታል።
በአንድ ወቅት አንድ በደዊ❨የገጠር ሠው❩ ወደ አሏህ መልክተኛﷺ ዘንድ መጣና ፡ ❝ አንቱ የአሏህ ነቢይﷺ ሆይ!.. አሏህ በእኔ ላይ ግዴታ ያደረገው ፆም ምንድነው?❞ ብሎ ጠየቃቸው ።
እሳቸውም ﷺ፡❝ የረመዷን ፆም❞ በማለት መለሡለት።
📜 ቡኻሪ ሙስሊም ዘግበውታል።
የረመዳንን ፆምን ያለ ምክንያት የተወ ሰው ፍርድ
ـــــــــــــــــــــ❀•▣ ▣•❀ــــــــــــــــــــــ
ረመዳን ከኢስላም መሰረቶች አንዱና በኢስላም ግዴታ እንደሆኑ ሁሉም ሰው ከሚያቃቸው ግዴታዎች መካከል አንዱ ነው። ፆም የለም ብሎ የካደ ሰው ይከፍራል። ይከፍራል ማለት እንደ ሙርተድ ይሰተናገዳል ፡ ተውበት ያስደርጉታል ፡ ተውበት ካደረገ ይቀበሉታል ተውበት አላደርግም ካለም ይገደላል።
⛔️ይህም የሚሆነው ❨የሚገደለው❩ ወደ እስልምና ቅርብ ጊዜ የገባና ከኡለማ ርቆ የሚኖር ሰው ካልሆነ ነው።
የፆምን ግዴታነት ሳይክድ ያለምንም ምክንያት የረመዳን ፆምን የተወ ሰው ፡ ለምሳሌ :- “ ፆም ግዴታ ነው ግና አልፆምም “ ያለ ሰው ፋሲቅ ❨አመፀኛ❩ ይሆናል። ነገር ግን ካፊር አይሆንም።ሙስሊም በሆነ መሪ ላይ አስሮት ምግብና መጠጥን በቀኑ ክፍለ ጊዜ ሊከለክለው ግዴታ ይሆንበታል። ፆም ሚመስል ነገር እንኳን እንዲገኝለት( ተገዶ ሲፆም ኒያ ላይገኝ ስለሚችል) ።
የረመዳን ወር ፆም ያለ ምክንያት የተወ ሰው

💢ግዴታ መሆኑን ያልካደ
ፋሲቅ ወይም አመፀኛ ነው ፡ አይከፍርም በሙስሊም መሪ ላይ በቀኑ ክፈለ ጊዜ ሊያስረው ምግብ ሊከለክለው ግዴታ ይሆንበታል።
💢ግዴታ መሆኑን የካደ
ካፊር ይሆናል፤ እንደ ሙርተድ ይስተናገዳል ፤
ተውበት ያስደርገዋል..ተውበት ካደረገ ይቀበሉታል ያለበለዚያ ይገደላል።
የፆም ጥበቡ ፣ሚስጥሩና ጥቅሙ

♦️አንድ አማኝ የረመዷን ወር ፆም አሏህ ግዴታ ያደረገው ኢባዳ እንደሆነ ከሁሉም ነገር በፊት ሊያውቅ ይገባዋል። ኢባዳ ነው ሲባል ከፆም የሚገኙ የትኛውንም አይነት ጥቅሞችን ሳይመለከት የአሏህን ትእዛዝ ተቀብሎ መተግበር ማለት ነው።
꧁°•.❃_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_-_- ❃.•°꧂ ገፅ 1