በአስተምህሮት መልክ የመውሊድን መፈቀድ ከቁርአንና ከሃዲስ ካውጣጡልን ኡለሞች መካከል ኢማም ኢብኑ ሃጀር አልዓስቀላኒ ይገኙበታል ሃዲሱም: _
✍ ቡኻሪና ሙስሊም እንደዘገቡት " የአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم
ወደመዲና ሲገቡ አይሁዶች የዐሹራን ቀን ሲጾሙ አገኟቸዉና ለምን እንደሚጾሙ ሲጠይቋቸዉ፡- ‹‹አላህ ፊርዐዉንን አስጥሞ ሙሳን ያዳነበት ቀን ስለሆነ እርሱን ለማመስገን ስንል ዕለቱን በጾም እናሳልፈዋለን›› አሏቸዉ፡፡ ነብዩም፡- ‹‹ ለሙሳ እኛ ከናንተ ይበልጥ የተገባን ነን››
አሉና የዐሹራ ቀን እንዲጾም አዘዙ፡፡
📚 ሸይኹል ኢስላም እብንሀጀር አልዐስቀላኒ ይህን ሀዲስ ‹‹አስሉን ሳቢት›› /ለመዉሊድ መታሰቢያ ሸሪዐዊነት ጽኑ መነሻ/ ካሉት በኋላ ሁለት መሠረታዊ ትምህርቶች እንደሚቀሰሙበት ገልጸዋል፡፡ አነርሱም፡-
ሀ.አላህ በአንድ የታሪክ ወቅት ጸጋዉን በመለገስ ለዋለዉ ዉለታ
በየዓመቱ በልዩ ሁኔታ ማመስገን፣
ለ. ምስጋናዉ በጾምና በሌሎች ዒባዳዎች መገለጽ እንደሚችል፤ ኢማሙ
ይህን ካሉ በሁዋላ፡- ‹‹ነብዩ ከመወለዳቸዉ የበለጠ ለሰዉልጅ የተሰጠዉ ጸጋ የለም››በማለት የሚከተለዉን የቁርአን መልዕክት በዋቢነት ጠቅሰዋል፡-
" لَقَدْ مَنَّ ٱللَّهُ عَلَى ٱلْمُؤْمِنِينَ إِذْ بَعَثَ فِيهِمْ رَسُولًۭا مِّنْ أَنفُسِهِمْ يَتْلُوا۟ عَلَيْهِمْ ءَايَٰتِهِۦ وَيُزَكِّيهِمْ وَيُعَلِّمُهُمُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَإِن كَانُوا۟ مِن قَبْلُ لَفِى ضَلَٰلٍۢ مُّبِينٍ "
‹‹አላህ በምእምናን ላይ ከጎሳቸው የኾነን ፤በእነርሱ ላይ አንቀጾቹን የሚያነብ፣
የሚጠራቸውም መጽሐፍንና ጥበብን የሚያስተምራቸውም የኾነን መልእክተኛ
በውስጣቸው በላከ ጊዜ፤ በእርግጥ ለገሰላቸው፡፡ እነርሱም ከዚያ በፊት በግልጽ
ስህተት ውስጥ ነበሩ፡፡››
👉 የሸይኹል ኢስላም እብንሀጀርን ቃል እንደወረደ ልጥቀስ፡-
فُيستفاد منه فعل الشكر الله على ما منَّ به في يوم معين من إسداء نعمة أو
دفع نقمة، ويعاد ذلك في نظير ذلك اليوم من كل سنة والشكر الله يحصل
بأنواع العبادة كالسجود والصيام والصدقة والتلاوة ، وأي نعمة أعظم من
النعمة ببروز هذا النبي نبي الرحمة- عليه السلام - في ذلك اليوم
‹‹አላህ ጸጋ በመለገስ ወይም ጉዳትን በማስወገድ ለዋለዉ ዉለታ እንደ
ሱጁድ፣ጾም፣ሶደቃና ቁርአን መቅራት ባሉ ዒባዳዎች ምስጋና ማድረስና ይህ
ዉለታዉ የተፈጸመበትን ቀን እየጠበቁ በየዓመቱ ምስጋናዉን መደጋገም
ተገቢ መሆኑን ከዚህ ሀዲስ እንማራለን፡፡ ይህ የእዝነት ነብይ ከመወለዳቸዉ
የበለጠ ምን ጸጋ አለ?››
አል ሃዊ ሊልፈታዊ 201
ምንጭ: መውሊድ መፅሃፍ (ሃሰን ታጁ)
https://t.me/sufiyahlesuna href='' rel='nofollow'>