የግብ እውነታዎች
“""""""""""""""""""‟
በሕይወታችሁ ልትሰሩት ከምችሏቸው ቀንደኛ ስህተቶች መካከል ከግብ ውጪ የመኖር ሁኔታ ተጠቃሽ ነው፡፡ የግብ መኖር ብዙ ጥቅሞች እንዳሉት ሁሉ የግብ አለመኖርም ብዙ ጉዳቶች አሉት፡፡
የግብ ጥቅሞች
1. ትኩረት፡- ግብ ያለው ሰው የሚያስበውንም ሆነ የሚያደርገውን ነገር ከግቡ አንጻር ስለሚቃኘው የየእለት ኑሮውን በከፍተኛ ትኩረት የሚኖር ሰው የሚሆነው፡፡
2. አዎንታዊ ስሜትና አመለካከት፡- ግብ ያለው ሰው በየእለቱ አዎንታዊ ስሜት፣ አዎንታዊ አመለካከትና አዎንታዊ ጉልበት ያለው ሰው ነው፡፡ ማታ ሲተኛ የቀኑን የግብ ጉዞ ገምግሞ የመተኛት፣ ጠዋት ሲነሳ ደግሞ የእለቱን ግብ አስቦ የመውጣት ልምምዱ ከፍተኛ አዎንታዊነትን ይሰጠዋል፡፡
3. በራስ መተማመን፡- ግብ ያለው ሰው መቼ ከየት ተነስቶ አሁን የት እንደደረሳና መቼ የቱ ጋር እንደሚደርስ በሚገባ ስለሚውቅ ከፍተኛ የሆነ በራስ መተማመን ያለው ሰው ነው፡፡
4. ቆጣቢነት፡- ግብ ያለው ሰው የለውን የጊዜ፣ የገንዘብ፣ የስሜትና የመሳሰሉትን ሃብቶቹን ሳያባክን በሚገባ የሚጠቀም ሰው ነው፡፡
5. ተፈላጊነት፡- ግብ ያለውን ሰው ያለውን የከበረና ዓላማ-መር ሕይወት ብዙዎች ሊጠቀሙበት ስሚፈልጉ ተፈላጊነቱን ይጨምረዋል፡፡
አምስቱ “በፍጹሞች”!
1. በፍጹም ከግብ ውጪ አትኑሩ! - የሕይወታችሁን ዓላማ እወቁና ከዚያ አንጻር ግልጽ የሆነን ግብ አውጡ፡፡
2. በፍጹም “ቅንጥብጣቢ” ግቦችን ስትከተሉ አትኑሩ! - ከሕይወታችሁን ዋና ዓላማ ጋር የማይዛመዱ ጥቃቅንና የተበጫጨቁ ግቦችን ከመከተል ተጠበቁ፡፡
3. በፍጹም ሰውን የማስደሰት ግብ አታውጡ፡- የግችሁን መሳካት ሰዎችን (ቤተሰብ፣ የትዳር አጋር፣ ፍቅረኛ . . . ) ከማስደሰት ጋር ካነካካችሁት ከተደሰቱ ግባችሁን እንደመታችሁ፣ ካልተደሰቱ ደግሞ ግባችሁን እንዳልመታችሁ ይመስላችሁ በከንቱ ትደክማላችሁ፡፡
4. በፍጹም ቀን ገደብ ያልተቀመጠለት ግብ አታውጡ! - የቀን ገደብ የሌለው ግብ መነሳሳት የማይሰጥ ከመሆኑም በላይ መሳካቱና አለመሳካቱን መመዘኛ ነጥብ የሌለው ግብ ነው፡፡
5. በፍጹም ከግባችሁ አትመለሱ! - ግብ ካለ እንቅስቃሴ አለ፤ እንቅስቃሴ ካለ ደግሞ ሁል ጊዜ እንቅፋት አለ፡፡ ወደግባችሁ ስትሄዱ እንቅፋት ሲያጋጥማችሁና ስትወድቁ እንደገና ተነሱና ቀጥሉ፡፡
👉በየቀኑ ጠቃሚ መልእክቶችን፣ መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ በነፃ የምታገኟቸው አሪፍ የኮምፒውተር ሶፍትዌሮች፣ የቢዝነስ ሃሳቦች እና የገንዘብና የተለያዩ ሽልማቶችን ለማግኘት ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።
☄️Super Boost-up
Digital marketing and consultancy
☎️0908 222223 / 0914 949494
📱ቴሌግራም👉
https://t.me/Superboostupp📱ፌስቡክ ገጽ👉
https://www.facebook.com/SuperBoostUp?mibextid=NTRm0r7WZyOdZZsz https://www.facebook.com/SuperBoostUp🌐ዌብሳይት 👉
https://superboostup.com/📱ቲክቶክ👉
@superboostup' rel='nofollow'>tiktok.com/
@superboostup