✞ እስጢፋኖስ ሰማዕት
እስጢፋኖስ ሰማዕት ሊቀ_ዲያቆናት
ለምእመናን የተሾምክ
የአምላክህን ትእዛዝ በስራ የፈፀምክ/2/
የስምህ ትርጎሜ የክብር አክሊል ነው
እስጢፋኖስ ፀሐይ ገድልህ የሚያበራው
ስድብና ዛቻ በድንጋይ መወገር
አንተን አይለይህም ከክርስቶስ ፍቅር
አዝ-------------
ህዝብን እንድትመራ በወንጌሉ ፋና
የስምንት ሺህ ነፍስ ምግባር ልታቀና
አምላክ ከፍ አረገህ በከበረው ሹመት
ጸጋን ተጎናጸፍክ መንፈሳዊውን ሀብት
አዝ-------------
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በጥበብ ተሞልተህ
አንገትህን በማቅናት ወደሰማይ አይተህ
ከሙታን ተነሥቶ በክብር ያረገውን
በአብ ቀኝ ቆሞ አየህ ኢየሱስ
አዝ-------------
በኩረ ሰማዕታት ሊቀ ዲያቆናት
የቤትህ መሰረት ታንጿል በአለት
አይፈርስም አይወድቅም በመከራ ዋዕይ
ዋጋውን ስላየ ያለውን በሰማይ
አዝ-----------
ብድራትን ሁሉ እስጢፋኖስ አይቶ
ለፍቅር የሞተውን አከበረው ሞቶ
አትቁጠርባቸው ይህንን እንደ ኃጢአት
እያለ ለመነ ለጠላቶች ምህረት
ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
✥ 💚 @mezmurochh 💚 ✥
✥ 💛 @mezmurochh 💛 ✥
✥ ❤ @mezmurochh ❤ ✥
╰══•❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
እስጢፋኖስ ሰማዕት ሊቀ_ዲያቆናት
ለምእመናን የተሾምክ
የአምላክህን ትእዛዝ በስራ የፈፀምክ/2/
የስምህ ትርጎሜ የክብር አክሊል ነው
እስጢፋኖስ ፀሐይ ገድልህ የሚያበራው
ስድብና ዛቻ በድንጋይ መወገር
አንተን አይለይህም ከክርስቶስ ፍቅር
አዝ-------------
ህዝብን እንድትመራ በወንጌሉ ፋና
የስምንት ሺህ ነፍስ ምግባር ልታቀና
አምላክ ከፍ አረገህ በከበረው ሹመት
ጸጋን ተጎናጸፍክ መንፈሳዊውን ሀብት
አዝ-------------
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በጥበብ ተሞልተህ
አንገትህን በማቅናት ወደሰማይ አይተህ
ከሙታን ተነሥቶ በክብር ያረገውን
በአብ ቀኝ ቆሞ አየህ ኢየሱስ
አዝ-------------
በኩረ ሰማዕታት ሊቀ ዲያቆናት
የቤትህ መሰረት ታንጿል በአለት
አይፈርስም አይወድቅም በመከራ ዋዕይ
ዋጋውን ስላየ ያለውን በሰማይ
አዝ-----------
ብድራትን ሁሉ እስጢፋኖስ አይቶ
ለፍቅር የሞተውን አከበረው ሞቶ
አትቁጠርባቸው ይህንን እንደ ኃጢአት
እያለ ለመነ ለጠላቶች ምህረት
ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
✥ 💚 @mezmurochh 💚 ✥
✥ 💛 @mezmurochh 💛 ✥
✥ ❤ @mezmurochh ❤ ✥
╰══•❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥