ብሔራዊ መታወቂያ ያልያዘ ተማሪ በቀጣይ ትምህርት ቤት አይመዘገብም ተባለ።
ከ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተማሪዎች ብሔራዊ መታወቂያ ካልያዙ መመዝገብ እንደማይችሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፤ ከ450 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ብሔራዊ መታወቂያ ለመመዝገብ የአንድ ወር ዘመቻ መጀመሩን ተናግረዋል።
ዋና ሥራ አስኪያጁ የከተማ አስተዳደሩ ለምዝገባው አስፈላጊውን የሰው ኃይል እና የቁሳቁስ ዝግጅት አጠናቅቆ ወደ ተግባር መግባቱን ገልጸዋል፡፡
በመዲናዋ ለሚገኙ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ብሔራዊ መታወቂያ ለማዳረስ ምዝገባው ከትምህርት ቤቶች ባለፈ በሁሉም የከተማ አስተዳደሩ መዋቅሮች አንደሚካሄድም አስታውቀዋል፡፡
ቤተሰብም በቀጣዩ የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ብሔራዊ መታወቂያ መያዝ እንዳለባቸው አውቆ በተዘረጉት አማራጮች ሁሉ ልጆቹን እንዲያስመዘግብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
©Ethio FM
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
https://t.me/temhert_bebete