በአገራችን ጎልተው የሚታዩትን የጤና ችግሮች ለመዋጋትና ለመከላከል የሚችሉ የጤና ሙያተኞችን በአጭር ጊዜና በቀላል ወጭ ለማሰልጠን ታልሞ በ1947ዓ.ም የተቋቋመው የጎንደር የሕዝብ አጠባበቅ ኮሌጂና ማሰልጠኛ ተቋም ሥራውን ሲጀምር በሦስት ፕሮግራሞች ማለትም በጤና መኮንኖች፣ በኅብረተሰብ ነርሶችና የጤና አጠባበቅ ተቆጣጣሪዎች ብቻ ነበረ። እነዚህም ሦስቱ የጤና ሙያተኞች የጎንደር መሠረታዊ የጤና ቡድን በመባል ይታወቁ ነበረ።
በአሁኑ ሰዓት የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በቅድመ ምረቃ፣ በማስተርስ፣ በፒኤችዲ፣ በስፔሻሊቲ እና ሰብስፔሻሊቲ ከ100 በላይ ፕሮግራሞች አንቱ የተባሉ አያሌ ኃኪሞችንና የጤና ባለሙያዎችን ለአገራችንና ለዓለም አበርክተናል።
ዛሬ የበዓሉ ታዳሚዎች እኛ ብንሆንም በህይወት ኖረው ከመካከላችን ያልተገኙ፤ እንዲሁም በህይወት የሌሉ ትውልዶች ሁሉ የዩኒቨርሲቲያችን ሰባት አስርት ዓመታት ታላቅ የአገልግሎት ጉዞ፤ እንዲሁም ለአንድ ክፍለ-ዘመን ያህል ያልተቋረጠ፤ በተግዳሮቶች ተፈትኖ ያልወደቀ፤ በትውልድ ቅብብሎሽ አሁን ከሚገኝበት ታላቅ ክብር ላይ እንዲደርስ ላደረጉ አባቶችና እናቶች ክብርና ምስጋና ይድረሳቸው።
Asrat Atsedeweyn, PhD
President, UoG