# tsedekenews //ሚያዝያ 5/2017ጠዋት ዓላም በፀደቀ እይታ ዜናዎች
# tsedekenews //
መንግሥት የሰብዓዊ ዕርዳታ ፈላጊዎችን ቁጥር 86 በመቶ ቀንሻለሁ ብሏል።
በየዓመቱ ከውጭ ይመጣ የነበረ አንድ ቢሊዮን ዶላር ማዳኑንም ገልጿል።
ባለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ዕርዳታ ፈላጊዎችን ቁጥር በ86 በመቶ መቀነሱን፣ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ጋር፣ በኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ረቂቅ አዋጅ ላይ የአስረጂና የባለድርሻ አካላት መድረክ ውይይት ሲደረግ ነው ይህ የተገለጸው፡፡ረቂቁን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለ ማሪያም (አምባሳደር)፣ ‹‹ባለፉት አምስት ዓመታት ጨዋታ ቀያሪ የሆነ ወረቶችን ማስመዝገብ ችለናል፤›› ካሉ በኋላ፣ ‹‹በትልቅ ስኬትነት የምናቀርበው ባለፉት አምስት ዓመታት የሰብዓዊ ዕርዳታ ፈላጊዎችን ቁጥር እስከ 86 በመቶ የቀነሰበት
ነባራዊ ሁኔታ መፈጠሩን ነው፤›› ብለዋል፡፡፡(ራፖርተር ዘግቧል )
# tsedekenews //
የወንድ የዘር ፍሬ የሩጫ ውድድር በአሜሪካ ሊካሄድ ነው ተባለለመጀመሪያ ጊዜ የወንድ የዘር ፍሬ ውድድር ግንቦት 2 በካሊፎርኒያ የሚካሄድ ሲሆን፣ ከሁለት ዩኒቨርሲቲዎች ማለትም ከዩኤስሲ እና ከዩሲኤልኤ የተወሰዱ ናሙናዎች በአጉሊ መነጽር በሚታይ የመሮጫ ላይ ውድድር ይወዳደራሉ።
ዝግጅቱ በሆሊውድ ፓላዲየም ፊት ለፊት 5,000 ተመልካቾች በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን፣ የቀጥታ ስርጭት፣ ተንታኞች እና ውርርድም ይኖራል ተብሏል።
# tsedekenews //
የሆሳዕና በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ እየተከበረ ነውየሆሳዕና በዓል በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ በዛሬው ዕለት እየተከበረ ይገኛል።በዓሉ በአዲስ አበባ ቅድስት ልደታ ማርያም ካቴድራል የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል በተገኙበት በተለያዩ ስነስርዓቶች ተከናውኗል፡፡የሆሳዕና በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ በተለይም አረጋውያን፣ ሴቶች፣ ወንዶች፣ ወጣቶች እና ሕጻናት “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፣ ሆሳዕና በዓርያም” በማለት በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው፡፡
# tsedekenews//
አሜሪካ በአንዳንድ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ላይ የጣለችው አዲስ ታሪፍ የተወሰኑ ምርቶችን እንደማያካትት ተረጋገጠ[#tsedekenews ]ሲኤንቢሲ ኒውስ እንደዘገበው ወደ አሜሪካ የሚገቡ እንደ ስማርት ስልኮች፣ ኮምፒውተሮችና የመሳሰሉት በርካታ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች በቅርቡ በአሜሪካ መንግስት በታወጀው አዲስ የገቢ ቀረጥ
እንደማይጎዱ ተረጋግጧል።
ይህ ዜና እነዚህን ምርቶች ከአስመጪ ሀገራት ወደ አሜሪካ ለሚያቀርቡ ኩባንያዎች እንዲሁም በአሜሪካ ውስጥ ላሉ ሸማቾች እፎይታን የሚሰጥ ነው። መንግስት ይህንን ውሳኔ ያደረገበት ምክንያት እስካሁን በግልጽ ባይገለጽም፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በዘመናዊው ህይወት ውስጥ ያላቸውን ወሳኝ ሚናና በዋጋቸው ላይ ሊኖር የሚችለውን አሉታዊ ተፅዕኖ ከግምት ውስጥ ያስገባ ሳይሆን አይቀርም።
# tsedekenews
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/thejamalnews#the_ጀማል