የሚያዝያ 7 ቀን 2017 የዓለም ዜና
• በአማራ ክልል ከመንግሥት የሚዋጉ ታጣቂ ኃይሎች “ችግሮችን ለመፍታት ወደ ውይይት እንዲመጡ” የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ። ምክር ቤቱ ጥሪውን ያቀረበው የመንግሥት የጸጥታ አስከባሪዎች ከፋኖ ታጣቂዎች የሚያደርጉት ውጊያ ሁለተኛ ዓመቱን ሊደፍን በተቃረበበት ወቅት ነው።
• በደቡብ ሱዳን እየተባባሰ በመጣው ግጭት ካለፈው መጋቢት ወዲህ ከ200 በላይ ሰዎች መገደላቸውን እና ከ125,000 በላይ የሚገመቱ ሰዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ። ድርጅቱ ዛሬ ማክሰኞ ባሰራጨው መግለጫ ከአየር በተፈጸመ ድብደባ ብቻ ከ180 በላይ ሰዎች መገደላቸውን፤ ከ250 በላይ መቁሰላቸውን ይፋ አድርጓል።
• ሶማሊያ ከ56 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለምርጫ ድምጽ ሰጪዎችን መመዝገብ ጀመረች። ዛሬ የተጀመረው የድምጽ ሰጪዎች ምዝገባ መንግሥታት የሚያወጧቸውን ሕግጋት የሚያሟሉ ዜጎችን የመምረጥ መብት ወደሚያረጋግጥ ዓለም አቀፍ አሠራር ሶማሊያን አንድ እርምጃ የሚያቀርብ ነው።
• በሱዳን አስገድዶ መድፈር እንደ ጦር ሥልት ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሚገኝ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስጠነቀቀ። ዛሬ ሁለተኛ ዓመቱን የደፈነው የሱዳን ጦርነት እንዲቆም የአፍሪካ ኅብረትን ጨምሮ የዓለም ሀገራት ጥሪ አስተላልፈዋል።
• እስራኤል በጋዛ ሠርጥ በሚገኘው የኩዌት የመስክ ሆፒታል ደጃፍ በፈጸመችው የአየር ጥቃት አንድ የሕክምና ባለሙያ ሲገደሉ በርካቶች ቆሰሉ። ጥቃቱ የተፈጸመው በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተበታተኑ የድንኳን መጠለያዎች በሚኖሩበት ሙዋሲ የተባለ አካባቢ ነው።
• አልጄሪያ አስራ ሁለት የፈረንሳይ ዲፕሎማቶች ለማባረር ያሳለፈችው ውሳኔ መዘዝ እንደሚኖረው የፈረንሳይ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አስጠነቀቀ። እርምጃውን "አሳዛኝ" ያሉት የፈረንሳይ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዦን ንዌል ባሮ ሀገራቸው የአልጄሪያን ውሳኔ በዝምታ እንደማታልፍ ዛሬ ማክሰኞ ተናግረዋል።
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇
https://t.me/thejamalnews
#the_ጀማል