#አጠቃላይየትምህርትአቂቅአዋጅ
በአገር አቀፍ፣ በክልል ወይም በአካባቢ ደረጃ ያለው የትምህርት ደረጃና ጥራት ከተጠበቀው በታች መወረዱ ሲረጋገጥ የሚመለከታቸው ፦
➡️ የፌደራል፣
➡️ የክልል
➡️ የአካባቢ የትምህርት አስተዳደር ኃላፊዎችን ተጠያቂ የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ ለፓርላማ ቀርቧል።
የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅ ባለፈው ሳምንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ተደርጎበት ለሰው ሀብት ልማት የሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ በአብላጫ ድምፅ ተመርቷል፡፡
ረቂቁ ምን ይዟል ?
🟢 የትምህርት ደረጃና ጥራት ከሚጠበቀው በታች የወረደ መሆኑ ሲረጋገጥ የትምህርት ተቋሙ፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው መምህራን፣ ሌሎች ለችግሩ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትና ግለሰቦች ተጠያቂዎች እንደሚሆኑ ተደንግጓል፡፡
🟢 በሒደቱ የትምህርት ደረጃና ጥራት መርማሪዎችን ሥራ ለማሰናከል የሚደረጉ ተግባራት የተከለከሉ መሆናቸው ተደንግጓል።
🟢 የአጠቃላይ የትምህርት ደረጃ ጥራትን በባለቤትነት የሚያስጠብቅ የትምህርት ቁጥጥርና ክትትል አገልግሎት የሚሰጥ መንግሥታዊ ተቋም በትምህርት ሚኒስቴር ሥር እንደሚቋቋም ተካቶበታል፡፡
🟢 የመንግሥት ዋነኛ ተግባር ዕድሜው ለትምህርት የደረሰ ማንኛውም ሕፃን ለአጠቃላይ ትምህርት ያለውን መብት ተግባራዊ ማድረግ፣ ተማሪውም የአንደኛና መለስተኛ ትምህርቱን ለመከታተል ያለበትን ግዴታ መወጣቱን ማረጋገጥ ያስችላል።
🟢 በትምህርት ዘርፍ ለሚሳተፉ ባለሀብቶችና ሌሎች መንግሥታዊ ላልሆኑ አካላት፣ በአገሪቱ የኢንቨስትመንት ሕግና አግባብ ባላቸው ሕጎች መሠረት ማበረታቻ ይሰጣል።
🟢 ስለትምህርት ክፍያ አለመኖር በሚያብራራው አንቀጽ በማንኛውም የመንግሥት አጠቃላይ የትምህርት ተቋም ውስጥ በመደበኛው የትምህርት መርሐ ግብር ከሚማር ተማሪ ከወላጆች ወይም ከአሳዳሪዎች የትምህርት ክፍያ፣ የመማርያ መጻሕፍት ዋጋ ወይም የመመዝገቢያ ክፍያ መቀበል ክልክል ስለመሆኑ ተደንግጓል፡፡
🟢 ክልሎች በሚያወጠት ሕግ መሠረት ለሌሎች የትምህርት መሣሪያዎች የሚውል መጠነኛ ክፍያ ከተማሪ ወላጆች የመክፈል አቅም ጋር በተጣጣመ መንገድ ሊያስከፍሉ እንደሚችሉ ተደንግጓል። ድንጋጌው ቢኖርም ይህንን አላሟላህም ተብሎ ተማሪው ከትምህርት ገበታው እንዲለይ ማድረግ አይቻልም።
🟢 የቅድመ አንደኛ ደረጃ መግቢያ ከአራት ዓመት እስከ ስድስት ዓመት ሲሆን፣ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ዕድሜ ደግሞ ሰባት ዓመት ተደርጓል፡፡
🟢 ተማሪዎች ቢያንስ ሦስት ቋንቋዎችን እንዲማሩ እንደሚደረግ ተደንግጓል። እንግሊዝኛ ቋንቋ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ይሰጣል። እንዲሁም አንድ ተጨማሪ የውጭ ቋንቋ ክልሉ በሚመርጠው መሠረት ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮ በአማራጭነት እንዲሰጥ ይደረጋል።
🟢 ማንኛውም ሰው ተገቢው የማስተማር ሥራ ፈቃድ ሳይኖርው በአጠቃላይ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በመምህርነት ሊሠራ እንደማይችል የተደነገገ ሲሆን፣ ለዚህ የሚረዳና የሥራ ፈቃድ አሰጣጥን የተመለከተ ስታንዳርድ መመርያ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ይወጣል።
🟢 ከቅድመ ሥራ ሥልጠና በኋላ በመምህርነት የሚመደብ ሰው በቅድሚያ የሁለት ዓመት የትውውቅ ሥልጠና የመከታተልና ለዚህም የሚሰጠውን መመዘኛ ፈተና የማለፍ ግዴታ አለበት። ይህን ግዴታ ከተወጣ በኋላ በዚህ አንቀጽ የሥራ ፈቃድ እንደሚሰጠው ተደንግጓል፡፡
🟢 የመምህራን የሙያ ፈቃዱ በየሁለት ዓመቱ መታደስ ያለበት ሲሆን፣ ዕድሳቱ ከማንኛውም የፈቃድ ክፍያ ነፃ ተደርጓል፡፡ ይህ ዕድሳት ለመምህራን ደረጃ ዕድገት እንደሚረዳ ተቀምጧል፡፡
🟢 በውጭ አገር ማኅበረሰቦች የሚቋቋሙ ትምህርት ቤቶች ከሚያስፈልጋቸው በጀት በአገራቸው መንግሥት 30 በመቶ የሚደገፉ እንደሆኑ፣ ቀሪውን 70 በመቶ ራሳቸው መሸፈን የሚችሉ መሆናቸውን የሚያሳይ ማረጋገጫ ማምጣት አለባቸው።
🟢 ኢትዮጵያ ውስጥ በሚቋቋሙ የውጭ አገር ማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶችና ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን ከሚመለከተው አገር የሥራ ፈቃድ ማምጣት እንደሚገባቸው ተደንግጓል፡፡ (ሪፖርተር ጋዜጣ)
@tikvahethiopia