#Update
ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት (4:38 ላይ) ተከስቶ የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዋሽ 36 ኪሎሜትር ርቀት ላይ እንደሆነ የጀርመኑ የጂኦሳይንስ ሪሰርች ማዕከል ገልጿል።
መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.9 መመዝገቡን አሳውቋል።
በርካታ ሰዎች የዛሬው ከወትሮው የተለየ ነበር ብለዋል።
የመሬት መንቀጥቀጡ የነበረበት አካባቢ ያሉ ወገኖች " አስፈሪ " ሲሉ ገልጸዋል።
ንዝረቱ የተሰማባቸው አካባቢዎች ደግሞ ከወትሮው የተለየ እንደነበር ታውቋል።
ለአብነት አዲስ አበባ ብዙ ሰዎች ህንጻ ላይ የነበሩ ተሰምቷቸው መደናገጣቸውን ገልጸውልናል። ለተወሰኑ ሰከንዶች የቆየ ቢሆንም የህንጻ ንቅናቄ ስሜት ፣ የመንስታወት መርገፍገፍ እንደተመለከቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አንድ የቤተሰባችን አባል " 4ኛ ፎቅ ላይ በተቀመጥኩበት መስታወቱ ፣ የቤት እቃዎች ሲነቃነቁ፣ እኔም በተቀመጥኩበት በወትሮ በተለየ ንዝረት ሲሰማኝ ነበር " ብሏል።
ሌላ 12ኛ ፎቅ ላይ የነበረ የቤተሰባችን አባል " ያስፈራ ነበር " ሲል ክስተቱን አስረድቷል።
ከዚህ ባለፈ ንዝረቱ ከተሰባቸው ቦታዎች አንዱ የጅሌ ጥሙጋ አካባቢ ሲሆን የወረዳ አስተዳደር ህንፃ ላይ የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች በድንጋጤ ከህንጻው መውረዳቸውን ከሰራተኞቹ ለመረዳት ተችሏል።
Photo Credit - Omer Al Faruq
@tikvahethiopa