#ማብራሪያ
አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴስ ፈረንሳይኛ ቋንቋን ለማስተማር የኦንላይን ምዝገባ መጀመሩን ጥቆማ መስጠታችን ይታወሳል።
የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትም በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ጠይቀዋል። የኮርሱ አስተባባሪ ሜሌና ሳሙኤል ተጨማሪውን ማብራሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።
ምን አሉ ?
- ትምህርቱ በተለያየ የፈረቃ አማራጭ በሳምንት ለ 6 ሰዓት የሚሰጥ ነው። የአንድ ተርም ኮርሶችን ለመጨረስ 2 ወር ተኩል ይፈጃል። አጠቃላይ ትምህርቱን ለመጨረስም 3 አመት እንደሚፈጅና በ4 ደረጃዎች (level) መከፈሉንም አስተባባሪዋ ገልፀዋል።
- ትምህርቱ ጧት፣ ከሰዓት፣ ማታ እንዲሁም በመደበኛ እና በእረፍት ቀናት #ማንኛውም ቋንቋውን መማር ለሚፈልግ ሰው የሚሰጥ ነው ተብሏል።
- ትምህርቱ በፒያሳ እና ቦሌ ኦሎምፒያ የሚሰጥ ሲሆን በኦንላይን የሚሰጥበት አማራጭም መኖሩ ተጠቁሟል።
- ተማሪዎች ከአንድ ደረጃ ወደ ቀጣዩ ለመሻገር ከፈረንሳይ ሀገር የሚመጣ አለማቀፍ ፈተና በፒያሳ እንደሚፈተኑ ተገልጿል። ቋንቋውን ለመቻልም የተማሪ ጥረት ወሳኝ መሆኑና እንደተማሪው አቅም የሚወሰን መሆኑ ተገልጿል።
ክፍያው ምን ይመስላል?
- በመደበኛ ቀናት ለመማር የአንድ ተርም ክፍያ 4ሺ ብር ሲሆን መመዝገቢያው 500 ብር ነው።
- በእረፍት ቀናት ለአንድ ተርም 4ሺ 500 ብር ነው ተብሏል። በቦሌ ኦሎምፒያ ለመማር ክፍያው 5ሺ ብር መሆኑም ተነግሯል።
- ተማሪዎች ለ1 ደረጃ (level) ለሚገለገሉበት መማሪያ መጻሕፍት 1800 ብር ክፍያ እንደሚከፍሉም ተገልጿል።
@tikvahethmagazine