" በመጪዎቹ ወራት በቆላማው የሶማሌ፣ የኦሮሚያ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ድርቅ ይከሰታል " - ዩኒሴፍ
በኢትዮጵያ በመጪዎቹ ወራት በቆላማው የሶማሌ፣ የኦሮሚያ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች "ላ ኒና" በተሰኘው የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ድርቅ እንደሚከሰት ዩኒሴፍ ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ።
"ላኒ-ና" ከጥቅምት እስከ ታህሳስ ባለው የዝናብ ወቅት ድርቅ እንደሚያመጣ ይጠበቃል ያለው ሪፖርቱ በተጠቀሱት አካባቢዎች ከአማካይ በታች ዝናብ እንደሚዘንብ ተንብዪዋል።
ይህም ሁኔታ የውሃ እና የግጦሽ አቅርቦት ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድር፣ የምግብ ዋስትናን እንደሚያባብስ እና እንደ ኮሌራ እና የኩፍኝ ወረርሽኝ ያሉ የህዝብ ጤና ስጋቶችን እንደሚባባሱ ሪፖርቱ አመልክቷል።
በተቃራኒው የመስከረም-ጥቅምት የመኸር ወቅት፣ በመላ ሀገሪቱ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች አጣዳፊ የምግብ ዋስትና እጦትን ቀስ በቀስ እያሻሻለ ነው ተብሏል።
ዩኒሴፍ በመላ ሀገሪቱ ከነሐሴ እስከ መስከረም ባለው ጊዜ ከ94,000 በላይ በከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለተቸገሩ ህጻናት ድጋፍ መስጠቱ ተመላክቷል።
ዩኒሴፍ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦትን ለመደገፍ 535 ሚሊዮን ዶላር እንደሚፈልግ ያመለከተው ሪፖርቱ እስከ መስከረም ባለው ጊዜ ያገኘው የገንዘብ ድጋፍ 116 ሚሊዮን ዶላር ነው። ይህም 78 በመቶ የገንዘብ ድጋፍ እጥረት እንዳለበት በሪፖርቱ ገልጿል።
@tikvahethmagazine