የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ከአውሮፓ ውጭ የሚመጡ ዜጎች ቤት እንዳይገዙ ሊከለክሉ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ስፔን የገጠማትን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመቅረፍ ከአውሮፓ ውጭ የሚመጡ ዜጎች በሀገሪቱ በቶችን እንዳይገዙ በከፊልና ሙሉ በሙሉ የሚያግደውን እቅድ ይፋ አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ''ስፔን ውስጥ ቤተሰብ ኖራቸውም አልኖራቸውም ከአውሮፓ ውጭ የመጡ ዜጎች በኛ ሀገር ቤት መግዛት አይችሉም'' ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ይህንን እና በውጪ ዜጎች የንብረት ይዞታ ታክስ ላይ ያለውን ታክስ በ100 % ለማሳደግ ጭምር እቅድ ያስቀመጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እቅዳቸው ገና ወደ ህግ አውጪው ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ይጠበቃል።
ባለፈው ዓመት በስፔን ነዋሪዎች መኖሪያ ቤቶችን ለማግኘት በመቸገራቸው ምክንያት የተቃውሞ ሰልፎችን ስፔን ተመልክታለች።
ማድሪድን ጨምሮ በታዋቂ ከተሞች የኪራይ ዋጋ መናር የአካባቢው ነዋሪዎች ከስፔን ገበያ ውጪ እየተደረጉ እንደሆነ እንዲሰማቸው አድርጓል።
በስፔን ውስጥ ከሚሸጡት አምስት ቤቶች ውስጥ አንዱ በውጭ ዜጎች የሚገዛ ሲሆን ብዙዎቹም ነዋሪ ያልሆኑ ናቸው።
ከአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ውጭ የሆኑ ዜጎች በ2023 ብቻ 23,000 ቤቶችን መግዛታቸው ተሰምቷል፡፡
Credit : Reuters, Independent
@tikvahethmagazine