#Somalia 🇸🇴
የአልሸባብ ታጣቂዎች በሶማሊያው ፕረዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ ላይ በዋና ከተማይቱ ሞቃዲሾ የቦምብ ጥቃት ማድረሳቸው ተሰምቷል።
ሁለት ከፍተኛ የመንግስት እና ወታደራዊ ባለስልጣናት ለሮይተርስ እንዳረጋገጡት ፕረዚዳንቱ ጥቃቱን ተከትሎ ደህና መሆናቸውን ገልጸዋል።
ጥቃቱን የተመለከቱ ወታደሮች እና የአካባቢው ነዋሪዎች የፕረዚዳንቱ ኮንቮይ መምታቱን አረጋግጠዋል። የሮይተርስ ጋዜጠኛ በቦታው በተገኘበት ሰዓትም በፕረዚዳንቱ ቤተ መንግስት አካባቢ በደረሰው ጥቃት የአራት ሰዎች አስከሬንን መመልከት ችሏል።
አልሸባብ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ባለው የቴሌግራም ቻናል ላይ ባሰፈረው መግለጫ "የእኛ ተዋጊዎቻችን ሀሰን ሼክ መሀመድን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከፕሬዚዳንት ቤተ መንግስት ለቀው ወደ አየር ማረፊያ ሲሄዱ ኢላማ አድርገናቸዋል" ይላል።
የሶማሊያ መንግስት ባወጣው መግለጫ ጥቃቱ መፈጸሙን ገልጾ ፕረዚዳንቱ ግን ሰላም መሆናቸውንና በጉዟቸውም አልሸባብን እየተዋጋበት በሚገኘው በመካከለኛው ሸበሌ አደን ያባል ግዛት ካሉ ወታደሮችን ጋር አቦሮ ለማፍጠር እንደነበርና በቦታውም እንደተገኙ ገልጿል።
@Tikvahethmagazine @tikvahmagbo