#Update 🇸🇸
የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሆኑት መሐመድ ዩሱፍ የደቡብ ሱዳንን ውጥረት ለማርገብ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር ተወያይተዋል።
የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበሩ በቀጣይ ለሰላም ተልዕኮ ከህብረቱ ተወካዮች የተወጣጣ ከፍተኛ ቡድን ወደ ጁባ እንደሚልኩ የገለፁ ሲሆን እነማን እንደሚላኩ ግን ይፋ አልሆነም።
የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር መሐመድ ዩሱፍ ከሳልቫ ኪር ጋር በደቡብ ሱዳን ያለውን ውጥረት ለማርገብ የውይይት አስፈላጊነት ላይ መምከራቸውም ተነግሯል።
የህብረቱ ሊቀመንበር እና ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ውይይት የተደረገው ለሰላም ተልዕኮ ወደ ጁባ አምርተው የነበሩት ራይላ ኦዲንጋ ከሪክ ማቻር ጋር ተገናኝተው እንዳያወሩ መከልከላቸውን ካሳወቁ በኋላ ነው ተብሏል።
ራይላ ኦዲንጋ ሪክ ማቻር ከከፍተኛ የጦር መሪ ግድያ ጋር በተያያዘ ምርመራ ላይ እንደሆኑ በደቡብ ሱዳን የመንግስት አካላት እንደተነገራቸው አሳውቀው ነበር።
@Tikvahethmagazine @tikvahmagbot