በኬንያ ጉንዳኖችን ደብቀው ከሃገር ሊያስወጡ የነበሩ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ከሃገር ሊወጡ የነበሩት ጉንዳኖች በአፍሪካ የሚገኙት ትላልቆቹ ጉንዳኖች እንደሆኑ ሲገለፅ እያንዳንዳቸው እስከ 220 ዶላር በእንግሊዝ ሻጮች በኩል እንደሚሸጡም ተገልጿል።
ግለሰቦቹ ጉንዳኖቹን በሲሪንጅ እና ትናንሽ ቱቦዎች ይዘው ሊወጡ የሞከሩ ሲሆን በእያንዳንዱ ቱቦ ውስጥ ሁለት ወይም ሶስት ጉንዳኖች እንደነበሩ እና ውስጡ ያለው ነገር እንዳይታወቅ በጥጥ ሸፍነውት እንደነበር አገልግሎቱ ገልጿል።
የጉንዳኖቹ መዳረሻ አውሮፓ ወይም እስያ እንደነበር ሲገለፅ የተያዙት ግለሰቦች ሁለቱ ቤልጂየማውያን፣ አንድ ቬትናማዊ እና ኬንያዊ መሆናቸው ተዘግቧል።
የዱር እንስሳት አገልግሎቱ ጉንዳኖቹ ከተወሰዱ በኋላ ልዩ መኖሪያ ወደ ተባለው ፎርሚካሪየምስ እንደሚኖሩ እና ቡድናቸውን ሲገነቡ ለመመልከት እንደሚፈልጓቸው ገልጿል።
ከኬንያ ሊወጡ ነበር የተባሉት ጉንዳኖች ሜሶር ሴፋሎቲስ ተብለው የሚታወቁ ሲሆን ወንዱ እስከ 20 ሚሊ ሜትር ሴቷ ደግሞ እስከ 25 ሚሊ ሜትር እንደምታድግ ተነግሯል።
Source : BBC
@Tikvahethmagazine @tikvahmagbot