ዶክተር አንቶኒ ሌቫቲኖ ከአንድ ሺህ ሁለት መቶ በላይ ፅንሶችን የማውረድ ሥራ የሠራ ሐኪም ነው፡፡ ይህንን ሥራ እየሠራ ግን በትዳር ሕይወቱ ልጅ ስላልነበራቸው ከሚስቱ ጋር ተስማምተው በማደጎ ልጅ ወስደው ማሳደግ ጀምረው ነበር፡፡ ልጅ ለማሳደግ ከተቀበሉ በኋላም ሚስቱበድንገት ጸነሰች፡፡ በማደጎ የወሰድዋት የመጀመሪያ ልጃቸው ስድስት ዓመት ሲሆናት በጁን 23 ከምሽቱ 1፡25 በተፈጠረ አደጋ ሴት ሕፃን ልጁ ትሞታለች፡፡ በዚህ ምክንያት ልቡ በጥልቅ ኀዘን ይሰበራል፡፡ ከኀዘን ዕረፍት በኋላ ወደ ሥራው ተመልሶ እንደተለመደው ፅንስ የማውረድ ሥራውን ከሠራ በኋላ የሆነውን እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፡፡
‘ውርጃውን አከናውኜ ከማሕፀን የወጣውን የፅንሱን አካል ባየሁ ጊዜ የታየኝ የእናቲቱ የመውለድና አለመውለድ መብት ወይንም በችግርዋ የረዳሁዋት ታላቅ ሐኪም መሆኔ አልነበረም፡፡ በዚያን ዕለት የታየኝ በዓሥራ አምስት ደቂቃ ሥራ የማገኘው የስምንት መቶ ዶላር ክፍያ አልነበረም፡፡ ያን ቀን በዚያ የታየኝ የሆነን ሰው ወንድ ልጅ ወይም ሴት ልጅ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ይህንን ሥራ ደግሜ ላለመሥራት ወሰንሁ’’
ሰልፍ የሚወጣላቸው ወገን የሌላቸው ሕፃናት ደም በእኛም ሀገር ይፈስሳል፡፡ ዛሬም ሔሮድስ በሥራ ላይ ነው፡፡ በዚህ መንገድ የሔድን ንስሓ እንግባ ፤ ያልሔድንበትም ሕፃናትን እንተዋቸው ወደ ምድር ይመጡም ዘንድ አንከልክላቸው፡፡ ይህችም ዓለም ለእነርሱ ናትና፡፡
#ክርስቲያኖች ሆይ ውለዱ!
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የካቲት 5 2012 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ቻናሌ መቀላቀል ለምትሹ
you tube
https://www.youtube.com/@1tewahdo
ቴሌግራም
https://t.me/tsidq