ከሀገር የሸሹ እና በሞት የተለዩ ተጠርጣሪዎችን ንብረት እንዲወረስ የሚያደርገው የንብረት ማስመለስ አዋጅ ተግባራዊ ሊደረግ ነው፡፡
ምንጩ ያልታወቀ ንብረትን በተመለከተ ተጠርጣሪው በሞት ቢለይ ወይም ከሀገር የሸሸ ቢሆንም ንብረቱ እንዲታገድና ጉዳዩ ተጣርቶ ግለሰቡ በሌለበት እንዲወረስ እንደሚደረግ ተገለፀ፡፡
በአዲሱ የንብረት ማስመለስ አዋጅ በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሰረተ የንብረት ማስመለስ አዋጁ እንደሚያካትት ሲገለፅ ይህም ተጠርጣሪው በሞት ቢለይ ወይም ከሀገር የሸሸ ቢሆን ንብረቱ እንዲሁ የሚቀር ሳይሆን እንዲታገድና ጉዳዩ ተጣርቶ ግለሰቡ በሌለበት እንዲወረስ ይደረጋል ሲል ፍትህ ሚኒስትር አስታውቋል።
የጸደቀው የንብረት ማስመለስ አዋጅ ተፈጻሚ ሲሆንም ምክንያታዊ ያልሆኑ ክሶች እንዳይመጡ ተጠርጣሪው ግለሰብ ስለ ጉዳዩ ቀርቦ እንዲያስረዳ ዕድል የሚሰጥና በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ብቻ ተፈጻሚ የሚሆን ነውም ብሏል።
አዋጁ በህገ-ወጥ መንገድ በወንጀል የተገኘ ንብረትን በአግባቡ በማስመለስ የሀገርንና የህዝብን ሀብት ከወንጀል ለመጠበቅ የሚሰራበት ነው ተብሏል።
የማይመለስ ጉዳት ማለትም ንብረቱ ከሃገር ሊሸሽና ሌሎች ተመሳሳይ ጉዳት ደርሶ ከሆነ ጊዜያዊ እግድ በራሱ በፍትህ ሚኒስቴር ያለፍርድቤት ትዕዛዝ እንደሚሰጥም ተገልጿል።
አዋጁ አንድ ግለሰብ በቅን ልቦና ባለማወቅ ንብረቱ ህገ-ወጥ መሆኑን ሳያውቅ የገዛ ቢሆን ንብረቱ እንዳይወረስ ተገቢውን ጥበቃ የሚሰጥ ነው ተብሏል።
በአዋጁ ላይ በተደነገገው መሰረትም ህገ-ወጥ ንብረት በማፍራት የተጠረጠረ ሰው ያለደረሰኝ በሰውም ሆነ ሌሎች ያስረዱልኛል ባላቸው ማስረጃዎች ጥፋተኛ አለመሆኑን ማስረዳት የሚያስችል መመሪያ እንዳለውም ተነስቷል።
አዋጁን ለማስፈጸም ከተለያዩ ሀገራት ጋር በትብብር የሚሰራ ሲሆን ንብረቱ ኢትዮጵያ ቢሆንም በውጭ ሀገራት በህገ-ወጥ መንገድ የተገኘ መሆኑ ከተረጋገጠ ለማስመለስ የሚሰራበት ነው ተብሏል።
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ⤵️
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ይህንን በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ ⤵️
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
ማስታወቂያ🔜@wasumohammed