የጤና ባለሙያዎች ፍትሃዊ ክፍያን ጨምሮ ሌሎች ጥያቄዎቻቸው ምላሽ እንዲያገኙ ጠይቁ‼️
የጤና ባለሙያዎች ፍትሃዊ የደመወዝ ክፍያ፣ የጤና መድን ሽፋን እና የተሻሉ ጥቅማጥቅሞች እንሟሉላቸው የሚጠይቅ የተቀናጀ 'የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ' መጀመራቸውን አስታወቁ።
ዶክተሮችን፣ ነርሶችን፣ ስፔሻሊስቶችን እና የቀዶ ጥገና ሐኪሞችን ጨምሮ የጤና ባለሙያዎች፤ "ህይወት ስናድን ኖረናል፤ አሁን የራሳችንን ህይወት ማዳን ይኖርብናል" የሚሉ ሃሽታጎችን በመጠቀም ጥያቄዎቻቸውን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች እያሰሙ ይገኛሉ።
አንድ የጤና ባለሙያ፤ "በዚህ ሰዓት የጤና ባለሙያው ለኑሮ ውድነት ተጋላጭ ሆኖ ነው ያለው። ሲያመው እንኳን ለመታከም የማይችልበትና ወደ ልመና የሚገባበት ክስተት ተፈጥሯል። የቤት ኪራይ እንኳን መክፈል አቅቶት መኖር ያልቻለበት ሁኔታ በመፈጠሩ ድምጻችንን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲሰማን ነው ንቅናቄውን የጀመርነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ሌላኛው የጤና ባለሙያ ለ5 ዓመታት ያህል በዘርፉ ሲሰሩ መቆየታቸውንና ወርሀዊ ደመወዛቸው 7600 ብር እንደሆነ ገልጸው በዚህም ምክንያት "ቤተሰብ እናትና አባቴን መርዳት ቀርቶ ራሴን መርዳት አልቻልኩም" ሲሉ አማረዋል።
📹 🔽
https://youtu.be/0ijXX752t0Y
https://youtu.be/0ijXX752t0Y
https://youtu.be/0ijXX752t0Y
የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🔽
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4