✞መድኃኒታችን✞
የምኞታችን ማረፊያ /መድኃኔዓለም መድኃኒት/(፪)
ምግብ ልብስና ቤታችን የኑሯችንም መሠረት
ትጉህ ኖላዊ ነው ነቅቶ የሚጠብቅ
ከተራራው ወርዶ ከበለስ ለበላች ለአንዷ የሚጨነቅ
ከአውሬ እየታደገ እንዳንመስል ዓለሙን
በመስቀል መንበር ላይ አዘጋችቶ ሰጠን ሥጋውና ደሙን
አዝ= = = = =
ጸጋችን ተገፍፎ ተራቁተን ብንርቅ
በቁም ሞትን ለብሰን በለስ አገልድመን በኃጢአት ብንደርቅ
በልጅነት ሥልጣን ከክብር ሊመልሰን
ከሸማኔ ጎድጓድ ከድንግል ተገኝቶ ራሱን አለበሰን
አዝ= = = = =
ከንቱ ቃል በመስማት ማረፊያ ስናጣ
ከገነት ተሰድደን ከሰማዩ መንግሥት ወደ ምድር ብንመጣ
ተድላና ርስት ሆኖ የምንወርሰው ሀገር
መንግስተ ሰማያት ወንጌልና ተስፋ እርሱ ነው እግዚአብሔር
መዝሙር
ዘላለም ታከለ ዘጎላ
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
የምኞታችን ማረፊያ /መድኃኔዓለም መድኃኒት/(፪)
ምግብ ልብስና ቤታችን የኑሯችንም መሠረት
ትጉህ ኖላዊ ነው ነቅቶ የሚጠብቅ
ከተራራው ወርዶ ከበለስ ለበላች ለአንዷ የሚጨነቅ
ከአውሬ እየታደገ እንዳንመስል ዓለሙን
በመስቀል መንበር ላይ አዘጋችቶ ሰጠን ሥጋውና ደሙን
መድኃኒታችን መድኃኔዓለም
የማያልቀው ምግብ ለተራበው ዓለም
አዝ= = = = =
ጸጋችን ተገፍፎ ተራቁተን ብንርቅ
በቁም ሞትን ለብሰን በለስ አገልድመን በኃጢአት ብንደርቅ
በልጅነት ሥልጣን ከክብር ሊመልሰን
ከሸማኔ ጎድጓድ ከድንግል ተገኝቶ ራሱን አለበሰን
መድኃኒታችን መድኃኔዓለም
የማያረጀው ልብስ ለታረዘው ዓለም
አዝ= = = = =
ከንቱ ቃል በመስማት ማረፊያ ስናጣ
ከገነት ተሰድደን ከሰማዩ መንግሥት ወደ ምድር ብንመጣ
ተድላና ርስት ሆኖ የምንወርሰው ሀገር
መንግስተ ሰማያት ወንጌልና ተስፋ እርሱ ነው እግዚአብሔር
መድኃኒታችን መድኃኔዓለም
የማይፈርስ ጽኑ ቤት ለፈላሲው ዓለም
መዝሙር
ዘላለም ታከለ ዘጎላ
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯