ኅዳር ፮ ቊስቋም ማርያም
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ቊስቋም ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓሏ በሰላም አደረሳችሁ ።
በዚህች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ አንዲሁም ከዮሴፍና ሶሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ 6 ወር በስደት ከተንገላታች በኋላ ወደ አገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው ።
ከግብጽ ሲመለሱ ጌታችን በእመቤታችን ጀረባ ላይ ሆኖ ጣቶቹ ወደ ኢትዮጵያ ይጠቁም ያመለክት ነበር፤ እመቤታችንም ልጄ ሆይ ለምንድነው ጣትህን የምታመለክተው ብትለው
"
ያቺ የተባረከች አገር ናት እኔን የሚያመልኩ አንቺን የሚማልዱ በፍቅርሽ የነደዱ ቅዱሳን መነኮሳት የሚፈልቁባት አገር ኢትዮጵያ ናት፤ በዚህች አገር ያሉ ሳይዩኝ ያመኑኛል፤ አስራት በኩራትሽ ትሁን ብሎ ሰጥቷታል፡፡በኪደተ እግራቸውም ጣና ሐይቅን ፤ ዋልድባንና ሌሎችንም ቦታዎች ዞረው እንደባረኩ ድርሳነ ኡራኤልና ተአምረ ማርያም ላይ በስፋት ተጽፏል፡፡
ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግስተ ሰማያት ስደት ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን::
©ልቦና ቲዩብ
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯