ወስያ (ኑዛዜን) የተመለከቱ ነጥቦች
1)ሙስሊም የሆነ ሰው ያለበትን እዳ እና እሱም ያበደረውን ፅፎ ሊያስቀምጥ ግዴታ አለበት።ቡኻሪ እና ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ﷺእንዲህ ብለዋል"አንድ ሙስሊም የሆነ ሰው ሊናዘዝበት የሚፈልገው ነገር ኖሮ ሳይፅፈው ሁለት ለሊቶችን ሊያድር አይገባም።
2)ከገንዘቡ የተወሰነውን ለመልካም ተግባር እንዲውል ቢናዘዝ ይወደድለታል።
👉ይህን ካደረገ ከሞተ በሇላም ምንዳው ይደርሰዋል
የአላህ መልእክተኛ ﷺእንዲህ ብለዋል"አላህ በምትሞቱ ግዜ በ1/3ኛ ገንዘባቹ ላይ ሰደቃ አድርጎላችሇል ምንዳችሁን እንድትጨምሩ።ስራችሁም እንዲጨምርላችሁ።
3)መናዘዝ ሚቻለው በ1/3ኛ ንብረት ወይም ከዛ በታች ባለው ነው።ከ1/3ኛ ንብረት በላይ መናዘዝ አይፈቀድም
4)ወራሼ የሌለው ሰው ግን ሙሉ ንብረቱን መናዘዝ ይችላል
5)ወራሽ ያለው ሰው ኑዛዜው ከ1/3 ቢያንስ የተመረጠ ነው።ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ ﷺ ለሰአድ ቢን አቢ ወቃስ 1/3ኛውም ብዙ ነው ብለውታል።
6)ብዙ ገንዘብ የሌለው እና ቤተሰቦችም ደሀ የሆኑበት ሰው ንብረቱን ለወራሽ ነው መተው ያለበት በንብረቱ ላይ ለሌላ አካል መናዘዝ የለበትም።
7)ብዙ ሀብት ኖሮት ቤተሰቦቹም ሀብታሞች ከሆኑ ቢናዘዝ ይወደድለታል
8)ለወራሽ መናዘዝ አይፈቀድም።ከውርስ ሚገባውን ስለተሰጠው።
👉የአላህ መልእክተኛﷺ እንዲህ ብለዋል
"አላህ ለሁሉም ባለሀቅ ሀቁን ሰጥቶታል ለወራሽ ኑዛዜ የለም።"
9)አብዛኞቹ ኡለሞች ዘንድ ወራሽ ላልሆነ የቅርብ ዘመድ መናዘዝ የተወደደ ተግባር ነው።
👉አብደላህ ቢን አባስ ግን ለማይወርስ ቅርብ ዘመድ መናዘዝ ግዴታ ነው ይላል።ምክንያቱም አላህ እንዲህ ብሏልና
كُتِبَ عَلَيْكُمْ إِذَا حَضَرَ أَحَدَكُمُ ٱلْمَوْتُ إِن تَرَكَ خَيْرًا ٱلْوَصِيَّةُ لِلْوَٰلِدَيْنِ وَٱلْأَقْرَبِينَ بِٱلْمَعْرُوفِ ۖ حَقًّا عَلَى ٱلْمُتَّقِينَ
አንዳችሁን ሞት በመጣበት ጊዜ ሀብትን ቢተው ለወላጆችና ለቅርብ ዘመዶች በበጎ መናዘዝ በናንተ ላይ ተጻፈ፡፡ (ይህ) በጥንቁቆቹ ላይ እርግጠኛ ድንጋጌ ተደነገገ፡፡
ሱራህ 2, አያህ 180
10)ኑዛዜው ተፈፃሚ ሚሆነው ያለበት እዳ ከተከፈ ዘካና ከፋራም ካለበት ከተከፈለለት በሇላ ነው።
11)የተናዘዘውን ኑዛዜ የመቀየር መብት አለው
12)ከ1/3ኛ ንብረቱ በላይ ከተናዘዘ ሚፈፀምለት በ1/3ኛ ንብረቱ ብቻ ይሆናል
13)በሀራም ነገር መናዘዝ አይቻልም
14)ሚናዘዘው ሰው አቅመ አዳም የደረሰ እና አእምሮ ጤነኛ መሆን ይኖርበታል
15)ወራሾችን ለመጉዳት ብሎ መናዘዝ አይፈቀድም
16)ኑዛዜው ተፈፃሚ ሚሆነው ሰውየው ከሞተ በሇላ ነው
17)ለካፊርም መናዘዝ ይቻላል
@yasin_nuru @yasin_nuru