"የውሻ ጩኸት ደመናን አይጎዳም!"
~~~~~~
በነብያችን ﷺ ላይ የሚሳለቅ እራሱን እንጂ እሳቸውን ምንም ሊያደርጋቸው አይችልም። የላካቸው አምላክ "መወሳትህን/ዝናህን ከፍ አደረግንልህ" ብሏቸዋል።
ይሄው የዝናቸው ከፍ ማለትም ነው ዛሬ በርካታ ውሾችን እያስጮኻቸው ያለው። ትላንትም የዛሬዎቹ ውሾች አያቶች የመልእክተኛውን ክብር ሊያንቋሽሹ ሞክረው ነበር። አላህ ግን እራሱ ለመልእክተኛው ﷺ ተከላካይ ጠበቃ ይሆንና መልእክተኛው ግን ነገሩን ንቀው እንዲተውት እንዲህ ይጠቁማቸዋል፡-
(فَٱصۡدَعۡ بِمَا تُؤۡمَرُ وَأَعۡرِضۡ عَنِ ٱلۡمُشۡرِكِینَ إِنَّا كَفَیۡنَـٰكَ ٱلۡمُسۡتَهۡزِءِینَ ٱلَّذِینَ یَجۡعَلُونَ مَعَ ٱللَّهِ إِلَـٰهًا ءَاخَرَۚ فَسَوۡفَ یَعۡلَمُونَ وَلَقَدۡ نَعۡلَمُ أَنَّكَ یَضِیقُ صَدۡرُكَ بِمَا یَقُولُونَ فَسَبِّحۡ بِحَمۡدِ رَبِّكَ وَكُن مِّنَ ٱلسَّـٰجِدِینَ وَٱعۡبُدۡ رَبَّكَ حَتَّىٰ یَأۡتِیَكَ ٱلۡیَقِینُ)
"የታዘዝክበትንም ነገር በይፋ ግለፅ፤ አጋሪዎችንም ተዋቸው። እኛ ተሳላቂዎችን ሁሉ በቅተነሃል። (እነሱም) እነዚያ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክን ያደረጉ ናቸው፤ በርግጥም (የስራቸውን ዋጋ) ወደፊት ያውቃሉ። አንተም በሚሉት ነገር ልብህ የሚጠብ መሆኑን በርግጥም እናውቃለን። ጌታህንም ከማመስገን ጋር አጥራው፤ ከሰጋጆቹም ሁን። እውነቱም (ሞት) እስከሚመጣህ ድረስ ጌታህን አምልክ።" [አልሒጅር 94-99]
ስለዚህ ተሳላቂዎቹ ውሾች ቢሳለቁም የነብያችን ﷺ ዝና የበለጠ ይገናል። የውሾቹ ስም ይከስማል። ውሻ ደግሞ ምን ታሪክ አለውና?!! እስኪ የነብያችንና የትላንት ጠላቶቻቸውን ዝና አወዳድሩ።
ሲጀመር መወዳደር ይችላሉ? በጭራሽ!! “የሰማይና የመሬት ያክል ነው” ብንል እንኳ በትክክል አይገልፀውም።
ግን የነብያችንን ﷺ ክብር ለማጉደፍ ተፍ ተፍ የሚሉ ሰዎች አላማቸው ምን ይሆን? መልሱ ግልፅ ነው።
1. አንዳንዶቹ በነብዩ ﷺ እውቅና ሂሳብ እውቅና መሸመት የሚፈልጉ ናቸው። “አንዳንዶች ታዋቂዎችን በመተቸት ታዋቂ መሆን ይፈልጋሉ” ሲባል አልሰማችሁም?
2. ሌሎቹ ደግሞ የኢስላም ውበቱና ሁለንተናዊነቱ የሚያስቀናቸው፤ ከፍተኛ ግስጋሴው የሚያስበረግጋቸው ናቸው። ስለሆነም ሙሐመድን ﷺ ሲያንቋሽሹ የኢስላም ውበቱ የሚደበዝዝ፣ ግስጋሴው የሚገታ ይመስላቸዋል። እውነታው ግን ተቃራኒው ነው። ኢስላም ዛሬ ጠላቶቹን እንቅልፍ በሚነሳ መልኩ በከፍተኛ ፍጥነት እየገሰገሰ ነው። ስለዚህ ውሾቹ አመል ሆኖባቸው ይጮሃሉ እንጂ የኢስላምን ግስጋሴ ሊገቱት አይችሉም!! ውሾቹ ይጮሃሉ፣ ዋው! ዋው!....።
ግመሉ ግን ጉዞውን ቀጥሏል። ውሻ ግመልን ማስቆም ከቻለች ትሞክር። ባይሆን ከኛ አንድ ነገር ይጠበቃል። ከሃዲዎችን የነብያችንን ﷺ ስም ለመዘለፍ ያበቃቸው ለነብዩ አስተምሮ ያላቸው ጥላቻ መሆኑ ይታወቃል።
አዎ የነቢዩ ﷺ ሱና እጅጉን ያስቆጫቸዋል!! እውነቱ ይህ ከሆነ ከሃዲዎችን የበለጠ ለማስቆጨት የሚጓጓ፤ ለሙሐመድ ﷺ እውነተኛ ወዳጅነቱን ማንፀባረቅ የሚፈልግ፣ ብሎም የአላህን ውዴታ ማትረፍ የሚሻ የበለጠ ወደ መልእክተኛው ሱና ይቅረብ፤ ትእዛዛቸውንም ይፈፅም፤ ከከለከሉትም ይራቅ። ይህን የሚያደርግ ጠላቱን የበለጠ ያስቆጫል። የአላህንና የመልክተኛውንም ﷺ ውዴታ ያፍሳል።
ያ ሱብሓላህ!!! የአላህና የመልክተኛውን ውዴታ ያገኘ ምን የቀረበት ነገር አለ?!!!! ያ ወሃ፞ቡ አንተ ወፍቀን!!! ኣሚን
@yasin_nuru @yasin_nuru