ከወር አበባ ጋር ተያይዞ የሚከሰት የስሜት መለዋወጥ
==========================
ከ80 እስከ 90 ከመቶ ሴቶች የወር አበባ ከመምጣቱ በፊት ያለው ሳምንት ላይ ምቾት አለመሰማት ያጋጥማቸዋል። መጠነኛ ራስ ምታት፣ የጡት መወጣጠር፣ ሆድ መነፋት ሊያግጥማቸው ይችላል። ልክ እንደ አካላዊ ለውጦች የስሜት ለውጦችም ይኖራሉ። መነጫነጭ፣ መከፋት፣ ከማህበራዊ ነገሮች ራስን ማግለል ...ወዘተ። እነዚህ ምልክቶች ብዙ ሴቶች ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ አያደርሱም። ይሁን እንጂ ከ20-30 አመቶ የሚሆኑት ላይ በስራቸው ወይም በትምህርታቸው ላይ ተፅእኖ ሊያመጣ ይችላል።
ይህ ህመም የሚያጋጥማት አንዲት ሴት የወር አበባ ከ15 አመቷ እስከ 50 አመቷ ብታይ በህይወቷ ይሄ ህመም 420 ጊዜ ያጋጥማታል ማለት ነው። ስለዚህ መፍትሄው ምንድነው?
1) ከወር አበባ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ህመምና የስሜት መለዋወጥ በህክምና የሚስተካከል ስለሆነ በዝምታ ከመሰቀያት ሀኪምን ማማከር።
2) ራስን መንከባከብ፣ እረፍት ማድረግ።
3) የወር አበባን ተከትሎ አንዳንድ ሴቶች ላይ የምግብ ፍላጎት ሊጨመር ወይም አንዳንድ ምግቦች ሊያምራቸው ይችላል። ሀይል ሰጪ (ካርሀይድሬት) የምግብ አይነቶች የድብርት ስሜትንና ጭንቀትን ስለሚያባብሱ በተቻለ አቅም መቀነስ።
4) ቫይታሚኖችን መውሰድ። አንዳንድ ቫይታሚኖችና ሚኒራሎች በተለይ ቫይታሚን ዲ እና ካልሺየም ከወር አበባ ጋር ተያይዞ የሚመጡ አካላዊና አእምሮዊ ምልክቶችን ለመቀነስ ያግዛሉ። ከሀኪም ጋር ተማክሮ መውሰዱ ጥሩ ነው።
ዶ/ር ዮናስ ላቀው
@yasin_nuru @yasin_nuru