አባት ከአምስት ሴት ልጆቹ ጋር ይኖራል
ለትዳርም ስለደረሱ አባት ከታላቋ ጀምሮ በቅደም ተከተላቸው እንዲያገቡለት ይፈልጋል
ታላቋ ግን አባቷን መንከባከብ በመፈለግ ማግባት አልፈቀደችም ታላቋ ብቻ ስትቀር አራቱ ልጆቹ አገቡ።
.
እሷም አባቷ አጀሉ ደርሶ እስኪሞት ድረስ ተንከባከበችው ። አባት ከሞተ በኃላ ግን ይቺ ሴት ብቻዋን ቀረች ።
የአባታቸውንም ኑዛዜ አገኙ እሱም " አደራ ራሷን መስዋዕት ያደረገችው እህታችሁ ሳታገባ ቤቱን እንዳትካፈሉ " የሚል ነበር.../
ነገርግን አራቱ እህቶች የትልቅ እህታቸውን ጉዳይ ቦታ ሳይሰጡ ተሽጦ መከፋፈልን ፈለጉ።
ትልቋ እህታቸው ቤቱን እንደሚሸጡት ስትረዳ ለመግዛት ለተስማማው ሰው በመደወል ከምትኖርበት ቤት ውጭ ሌላ እንደሌላትና ያለውን ሁኔታ አስረድታ ነገሮችን እስክታስተካክል ድረስ ጊዜ እንዲሰጣት አስፈቀደች ። ቤቱን የሚገዛውም ሰውም ፍቃደኝነቱን ገለፀላት።
ቤቱ ተሽጦ ለአምስቱ እህቶች ተከፋፈለ። ከተከፋፈለ በኃላ አራቱ ወደ ትዳራቸው ተመለሱ ታላቋ እህታቸው ከቤት ቀረች። ይቺ ሴት ወላጇን በመንከባከብ ባሳለፈችው ጊዜ አላህ ልፋቷን በዱንያም ከንቱ እንደማያስቀርባት ተማምና በአላህ ተስፋ አድርጋለች።
ወራት አለፉ ቤቱን ከገዛው ሰው ስልክ ተደወለላት ቤቱን እንድትለቅ መልክት እንደሚያስተላልፍ በመገመት በፍራቻ 'ይቅርታ እስካሁን ቤት አላገኘውም' አለችው።
እሱም ችግር የለም! የደወልኩም ለሱ ሳይሆን ቤቱን 'መህር' አድርጌ እንድታገቢኝ ልጠይቅሽ ነው ፍቃድሽ ከሆነ ባልሽ እሆናለው ፍቃደኛ ካልሆንሽም ችግር የለም! ቤቱ ግን ያንቺ ነው አላት ።
ይቺ ሴት አለቀስች! ተስማማችም አላህም የመልካም ሰሪዎችን ምንዳ ከንቱ አያስቀርምና በመልካም ተካሰች ።
አባቷን በተንከባከበችበት ቤት ትዳር ይዛ ባሏን መንከባከብ ጀመርች። 💍💍
ጌታችን ሆይ ! በየቤቱ ያንተን ተስፋ ብቻ የሚጠባበቁ እህቶች አሉና መልካምን ትዳር ወፍቃቸው/💍
@yasin_nuru @yasin_nuru