(የመጨረሻው ክፍል)
በተኛሁበት ልብሴ ፊቴን ሳልታጠብ ስራ ገባሁ። ማስተማር አይበለው! ሁኔታዬ ለራሴ ግራ እስኪገባኝ ድረስ ተለወጠ። እያስተማርኩ መንቀጥቀጥ ጀመርኩ። የተማሪው ፊት ሁሉ የናርዶስ ፊት መሰለኝ። ድምፃቸው ሁሉ ጎረነነብኝ።
"ሰርዬ እንዴ ሰር ምን ሆነህ ነው?"
"አረ ቢሮ ሰው ጥሩ ሰርዬ...
መሸሽ ፈለኩ። ወዴት እንደምሸሽ ግን አላውቅም። እየተከተለኝ ቢሆንስ? ምናልባት ውስጤ ቢሆንስ?
ተንገዳግጄ ወደ ኋላ ስወድቅ ብላክ ቦርዱ የተሰቀለበት ሚስማር አንገቴን የጎን ወጋው። ደሜ ተንዠቀዠቀ። ክላሱ ደም ለበሰ። የተማሪ ድንጋጤ፣ የተማሪ ጩኸት ለቅሶ በሰመመን ውስጥ ይታየኛል፤ ይሰማኛል። ናርዶስ አይኔ ድቅን አለች። በሃሳብ እይታዬን ጋረደችው። ፈገግ አለች። መድማቴ አስደስቷቷል፤ መውደቄ አርክቷቷል። ለነገሩ የሳቀችው እሷ አይደለችም እሱ ነው። ደም ነው የሚያስፈነጥዘው፤ ማቁሰል ነው የሚያፍነከንከው።
አፋፍሰው ትምህርት ቤቱ አካባቢ ወደሚገኘው ሆስፒታል ወሰዱኝ። ደሜ በቀላሉ የሚቆም አልነበረም። ከብዙ ርብርብ በኋላ ደሙን አስቁመው የተቀደደውን አንገቴን ከሰፉልኝ በኋላ ወደ ቤቴ ገባሁ።
ቶሎ ሊሻለኝ አልቻለም። ቁስሉ በቀላሉ የሚደርቅ አልሆነም። እለት እለት እንደ አዲስ ቁስል ይጠዘጥዘኛል። ሳምንታት ተቆጠሩ። ወራት እንደቀልድ አለፉ። በተደጋጋሚ ወደስራ እንድገባ ብጠየቅም እኔ ግን አቅም አጣሁ። በቦታዬ ሌላ ሰው ተቀጠረ፤ ልቤ ላይ ሃዘን ተተከለ። ከቤት ሳልወጣ 3 ወር ሞላኝ። እያንዳንዱ ቀን የአመት ያህል የረዘመ። እያንዳንዱ እንቅልፍ በቅዠት የተጠቀለለ። ፀሎት መፅሃፍ ታቅፌ ነው የምተኛው። ቅዠቱ ይቀልልኛል ለትንሽም ሰዓት ቢሆን አረፍ እላለሁ።
"አልናፈኩህም ወይ? መች ነው መተህ የምታየኝ?" አይኔን በጨፈንኩ ቁጥር፣ ለሊት መብራት በጠፋ ቁጥር ዙርያዬን የሚያቃጭል ድምጽ ነው።
"አልናፈኩህም ወይ?
መተህ አታየኝም?
በናፍቆትህ ነደድኩ እኮ? ተቃጠልኩ። ኡ ኡ ኡ ኡኡኡ ኡኡ ኡኡ ኡ ኡ ኡ ኡኡ
በጨለመ ቁጥር አይኔን በጨፈንኩ ቁጥር ጆሮዬ ላይ የሚጮህ ድምጽ።
አይኔን አልጨፍንም። ቀኑን ለሊቱን ሙሉ መብራት አላጠፋም። መብራት ሲጠፋ የሚገድሉኝ፤ አይኔን ስጨፍን የምሞት ይመስለኛል።
ፀሎት ላይ እስከዚህም ነኝ። ምን ብዬ እንደምፀልኝ አላውቅም። የሁልጊዜ ፀሎቴ አንተ እንዳልክ ይሁን ነው። ከዚህ የተለየ ፀሎት የለኝም። አልችም። አለመድኩም። ፆም ላይ ግን ብርቱ ነኝ። በምችለውም በማልችለውም የሚያስጨንቀኝን መንፈስ ታገልኩት።
አንድ ቀን አይኔን እንቅልፍ አሸነፈው። ፀሎት መፅሀፌን ታቅፌ አይኔን ጨፈንኩ። ስጨፍን ግን ያ የሚያስጨንቀኝ መንፈስ አልነበረም። ዝም ፥ እርግት ፥ ስክን ያለ ስፍራ። ዙርያውን በፅድ ዛፎች የተከበበ። አየሩ እጣን እጣን ፥ መኖር መኖር የሚሸት። ተረጋጋሁ።
ከወራት በኋላ ልቤ የሚረጋበት ቦታ አገኘ። ከፅዶቹ መሃል አንድ አባት እጃቸውን ወደ እኔ እየጠቆሙ ና ይሉኛል። ስጠጋቸው ይርቃሉ። ስጠጋቸው ስጠጋቸው የፅድ ጫካ ውስጥ ገብቼ የለበሱትን ልብስ ስነካ ባነንኩ። ይኸውልህ መሌ 12 አመት ሙሉ ደም ሲፈሳት የነበረች ሴት የክርስቶስን ልብስ ስትነካ ደሟ እንደቆመ ሁሉ እኔም እኚያ አባት የለበሱትን ልብስ ስነካ ጭንቀቴ ከላዬ የረገፈ ያህል ተሰማኝ።
መታደል ነው። ለካ ስትሞክር ነው የምትታገዘው። ለካ ስትጀምር ነው መንገድ የሚሰጥህ። መንገድ ተሰጠኝ። በህልሜ ያየሁትን ቦታ አቀዋለሁ። ከትውልድ መንደሬ አካባቢ ነው።
የዛሬ ወር ጉዞዬን በህልም ወዳየሁት ቦታ አደረኩ። በህልሜ ወደ ሰከንኩበት በአካልም ወዳማርፍበት ቦታ ሄድኩ። ከሶስት ሰባት በኋላ በአባቶች ብርቱ ፀሎት በፈጣሪም ፍቃድ ነፃ ወጣሁ። ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል። መሌ እዛ ምን እንደተፈጠረ ሌላ ጊዜ እነግርሃለሁ። ለአሁን ግን የነገርኩህን ፃፈው አስነብበው።
__
የጓደኛን ታሪክ ጓደኛ ይወርሳል። የመኖርን መንገድ ተጓዥ ይሄድበታል።
ታሪኩ ተጠናቋል እነደዚህ አይነት መሰል ታሪክ እንዲቀጥል ከፈለጉ በ Like አሳዩኝ በቀጣይ በሌሎች ታሪኮች እንገናኛለን