✞ የኛ አባት ሚካኤል
በቅድመ ሥላሴ በጉልበቱ ሰግዶ
ምስጋናን ያቀርባል የውዳሴን ነዶ
ምሕረትን ይዞ ከአምላክ ዘንድ ተላከ
ለማኑሄ ድርሳን ምስራች ሰበከ
አዝ___
ችግርን አልፋለሁ ይረሳል ሀዘኔ
በሕይወቴ ሠልፎች ስላለ ከጎኔ
ከአምላኬ ተልኮ የታደገኝ ከሞት
መርቶ ያደርሰኛል ከሠማዩ መንግስት
አዝ___
የአምላክ ስም በላዩ ስላለ ታትሞ
ከፊቴ ይወጣል በመንገዴ ቀድሞ
ያድናል ሚካኤል ጭንቀትን አርቆ
የወህኒውም መዝጊያ ይከፈታል አውቆ
አዝ___
ልጄ ነህ ብሎኛል አባቴ እለዋለሁ
ለአምላኬ ዘመርኩኝ ሲዘምር ስላየሁ
አይደክምም ልሳኑ አያውቅም ዝምታ
ምስጋና ምግቡ ነው ዘውትር ጠዋት ማታ
አዝ___
ስለህዝቡ ልጆች የሚነሳው መልዓክ
አንተነህ ሚካኤል የመረጠህ አምላክ
ዝማሬ ጸሎቴ አይሁንብኝ ከንቱ
ከእጣኑ ጢስ ጋር ይውጣልኝ በፊቱ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ሲያርፍ ያመሰግናል ሲያመሰግን ያርፋል
ሲያርፍ ያመሰግናል ሲያመሰግን ያርፋል
የኛ አባት ሚካኤል/2/ምሕረት ይለምናል
በቅድመ ሥላሴ በጉልበቱ ሰግዶ
ምስጋናን ያቀርባል የውዳሴን ነዶ
ምሕረትን ይዞ ከአምላክ ዘንድ ተላከ
ለማኑሄ ድርሳን ምስራች ሰበከ
አዝ___
ችግርን አልፋለሁ ይረሳል ሀዘኔ
በሕይወቴ ሠልፎች ስላለ ከጎኔ
ከአምላኬ ተልኮ የታደገኝ ከሞት
መርቶ ያደርሰኛል ከሠማዩ መንግስት
አዝ___
የአምላክ ስም በላዩ ስላለ ታትሞ
ከፊቴ ይወጣል በመንገዴ ቀድሞ
ያድናል ሚካኤል ጭንቀትን አርቆ
የወህኒውም መዝጊያ ይከፈታል አውቆ
አዝ___
ልጄ ነህ ብሎኛል አባቴ እለዋለሁ
ለአምላኬ ዘመርኩኝ ሲዘምር ስላየሁ
አይደክምም ልሳኑ አያውቅም ዝምታ
ምስጋና ምግቡ ነው ዘውትር ጠዋት ማታ
አዝ___
ስለህዝቡ ልጆች የሚነሳው መልዓክ
አንተነህ ሚካኤል የመረጠህ አምላክ
ዝማሬ ጸሎቴ አይሁንብኝ ከንቱ
ከእጣኑ ጢስ ጋር ይውጣልኝ በፊቱ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ