#ቃላትህ_እንደ_ወርቅ_ውድ_ይሁኑ!
ወርቅ የትም አይጣልምና
ሰሚ ሳታገኝ ዝም ብለህ አታውራ!
ቃላትህ እውነተኛ ዋጋ እንዲኖራቸው ከፈለግ፣ ከአፍህ የሚወጡበትን ትክክለኛ ጊዜ ምረጥላቸው። የጠቢቡን ቃልም አስታውስ "የወርቅ እንኮይ በብር ፃሕል ላይ፣ የጊዜው ቃል እንዲሁ ነው" ምሳ 25፥11
ያሳሰበህና መናገር የምትፈልገው ነገር ቢኖርም ለደከመውና ስራ ለበዛበት ወይም እረፍት ለሚፈልግና የማውራት ፍላጎት ላይ ላልሆነ ሰው አትናገር። ለተበሳጨና ለተከፋ ሰውም አትንገረው።
ጆሮዎች አንተን ለመስማት ዝግጁ በሆኑበት ጊዜ ብቻ አውራ። ምናልባት የተግሳጽ ቃል ካልሆነ በቀር።
መጥምቁ ዩሐንስም ሁልጊዜ አስታውስ! ቃልን ከአንደበትህ ማውጣት ያለብህ ሰሚ ጆሮ ስታገኝ ብቻ ነው! የሚል ንግግር አለው።
ብዙ የሚያወራ ግን አንዳች ጥቅም የማይገኝበት ሰው አይቻለሁ። ብዙ መናገሩ ቃላቱን ዋጋ ቢስ አድርጓቸዋል። የሚናገረው ነገር ስለሌለው፣ ሁሉንም ነገር ይናገራል፤ በቃ ዝም ብሎ ያወራል። ንግግሩ ግን ውጤታማ ነበር? አልነበረም። አዳማጮችም ጊዜያቸውን አባከኑ እንጅ አልተጠቀሙም።
አንተ ግን እንዲህ እንዳትሆን፤ ንግግር ሁሉ የተመዘነና የተመጠነ ይሁን። የምትናገረው ከሌለህ አታውራ፤ የምትናገረውን ለመስማት የተዘጋጄ ሳይኖርም አታውራ። ቃላት ለተጠቀመባቸው ትልቅ መሳሪያዎች ናቸው። ያጠፋሉ፣ ያለማሉ። ከሚያጠፉት አትሁን!

#ትምህርተ_ሺኖዳ መጽሐፍ
#አቡነ_ሺኖዳ_መልስ_አላቸው መጽሐፍ