በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የሳል ሽሮፕን መድኃኒት ከገበያ ላይ እንዲሰበሰብ መመሪያ ሰጡ
እ.ኤ.አ በ 2021 በጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተመረተው የህፃናት ሳል ሽሮፕ በስድስት የአፍሪካ ሀገራት የመድኃኒት ባለስልጣናት ከገበያዉ ላይ እንዲሰበሰብ ተደርጓል፡፡
ይህ የሆነው የናይጄሪያ መድሃኒት ኤጀንሲ ከፍተኛ መጠን ያለው መርዛማ እና ለሞት ሊዳርግ የሚችል ንጥረ ነገር እንደያዘ ካስጠነቀቀ በኋላ ነው።በታንዛኒያ እና በዚምባብዌ የሚገኙ የመድኃኒት ተቆጣጣሪዎች ሽሮፑ ላይ የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወሰድ በቅርቡ የጠየቁ ሲሆኑ የዚምባብዌ የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ሽሮፕ ወደ ሀገር ውስጥ ስለመግባቱ ምንም አይነት ማስረጃ የለም ግን ብሏል ።
ባለፈው ሳምንት የናይጄሪያ ብሔራዊ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር እና ቁጥጥር ኤጀንሲ (ናፍዳክ) በሽርፑ ውስጥ ዲቲሊን ግላይኮልን የተባለ መርዛማ ንጥረ ነገር እንዳለ በላብራቶሪ ከተረጋገጠ በኃላ የቤኒሊን የሕፃናት ሕክምና ሽሮፕ ከገበያዉ ላይ እንዲሰበሰብ ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወሳል፡፡ይህንኑ ተከትሎ ከጥቂት ቀናት በኋላ የኬንያ ፋርማሲ ቦርድ በናፍዳክ ምክር መሰረት የሽሮፑ ሽያጭ እንዲቆም ትዕዛዝ መሰጠቱን ዳጉ ጆርናል ከዘገባዎች ተመልክቷል፡፡
ከዚያም በደቡብ አፍሪካ እና በሩዋንዳ የመድኃኒት ባለስልጣናት ተከታትለዉ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ሽሮፑ እንዲሰበሰብ አዘዋል፡፡ዲቲሊን ግላይኮል በካሜሩን እና በጋምቢያ ውስጥ በቅርብ ጊዜ በደርዘን የሚቆጠሩ ህጻናት የሞት ምክንያት ሆኗል፡፡የሰው ልጅ ንጥረ ነገሩን መጠቀሙ በርካታ የጎንዮሽ ጉዳት የሚያስከትልበት ሲሆን አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳትን ጨምሮ ፣ ለሞት ሊዳርግ ይችላል።
ቤኒሊን የሕፃናት ሕክምና ሽሮፕ፣ ባች ቁጥር 329304 በደቡብ አፍሪካ በግንቦት 2021 የተመረተ ሲሆን ሚያዝያ 2024 የሚያበቃበት ቀን እንደሆነ ያለዉ ማስረጃ ያመላክታል፡፡የደቡብ አፍሪካው የመድኃኒት መቆጣጠሪያ ቡድን ባች 329303 መድኃኒቶች በደቡብ አፍሪካ፣ ኢስዋቲኒ፣ ሩዋንዳ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ እና ናይጄሪያ ተሽጠዋል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል