ሂዝቦላህ በሰሜናዊ እስራኤል በፈፀመው የሚሳኤል ጥቃት 10 ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ
👉 አንድ የእስራኤል ወታደር ተገድሏል
የእስራኤል የአምቡላንስ አገልግሎት እንዳስታወቀው በሰሜናዊ የእስራኤል ከተሞች ሃይፋ እና ጢቤሪያ በአንድ ሌሊት ከሊባኖስ በተተኮሰ ሚሳኤል 10 ሰዎች ቆስለዋል። አገልግሎቱ አክሎ እንዳስታወቀው ከቆሰሉት ሰዎች መካከል ሚሳኤል ሲተኮስ በመስታወት እና የመስኮት ፍርስራሾች ቆስለዋል። ሚሳኤሎቹ ሬስቶራንት ፣ መኖሪያ ቤት እና ዋና መንገድ ላይ መውደቃቸውን የገለፀው የእስራኤል ጦር በሄዝቦላህ የተተኮሱ ሚሳኤሎች የእስራኤልን የአየር መከላከያ ዘዴዎች እንዴት ሰብረው እንደገቡ በማጣራት ላይ ይገኛል ብሏል። ሄዝቦላህ ወታደራዊ ተቋማት ላይ እያነጣጠረ መሆኑን አስታውቋል።
የእስራኤል ጦር በሊባኖስ ከሂዝቦላህ ጋር እያደረገ በሚገኘው ጦርነት አንድ ወታደር ሲገደልበት ሌሎች ሁለት ወታደሮች ደግሞ ክፉኛ ቆስለዋል። የእስራኤል ጦር በሊባኖስ በኢራን በሚደገፈው ሂዝቦላህ ላይ የመሬት ወረራውን የጀመረው ባለፈው ሰኞ ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በተደጋጋሚ ድንበር ዘለል ውጊያ በማድረግ ላይ ይገኛል።በቀጠለው የእስራኤል ጦር እርምጃ በቤይሩት በከተማዋ ደቡባዊ ወረዳዎች ላይ ተጨማሪ ድብደባ የፈፀመች ሲሆን በወቅቱ ከፍተኛ ፍንዳታዎች ደርሰዋል። የእስራኤል ጦር የሂዝቦላህ ንብረት የሆኑ የጦር መሳሪያዎች ማከማቻ ቦታዎችን በመምታቱ ከፍተኛ ፍንዳታ ማድረሱን ገልጿል።
የእስራኤል ጦር ከሊባኖስ ውጪ በፍልስጥኤም ግዛቶች የሚፈፅመውን ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል።የእስራኤል መከላከያ ሃይል በማእከላዊ ጋዛ ሰርጥ ዲር አል ባላ በሚገኘው አል-አቅሳ ሆስፒታል ውስጥ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የሃማስ አባላት ላይ ጥቃት መፈፀሙን አስታውቋል። የመከላከያ ሃይሉ የሀማስ የማዘዣ እና የቁጥጥር ማእከላት ኢላማ ማድረጉን በመግለፅ ቡድኑ በእስራኤል የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ለማድረስ ይጠቀሙባቸው ነበር ብሏል።ከጥቃቱ በፊት ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ እርምጃዎችን መውሰዱን ገልጿል፣ ከእነዚህም መካከል “ትክክለኛ ጥቃት በቡድኑ አባላት ላይ ለመፈፀመ፣ የአየር ላይ ክትትል እና ተጨማሪ የስለላ መረጃ መጠቀሙን አስታውቋል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል