በሸገር ከተማ በዛሬው እለት በደረሰ የእሳት አደጋ እናት ከስድስት ወር ልጇ ጋር ህይወታቸው አለፈ
ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም በሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ-ከተማ በመስሪያና መሸጫ ሼድ ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ እናት ከስድስት ወር ልጇ ጋር ህይወቷ ማለፋን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
በእሳት አደጋዉ በሼድ ዉስጥ ካሉ ሱቆች መካከል ስድስት የንግድ ሱቆች ተቃጥለዋል። የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ሶስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ሁለት አምቡላንሶች ከሰላሳ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማራ ሲሆን የእሳት አደጋዉ ወደሌሎች ንግድ ሱቆች ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር መቻሉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።
ከንግድ ሱቆቹ መካከል በአንደኛዉ ነዳጅ በፕላስቲክ ጠርሙስ በችርቻሮ የሚሸጥበት ሱቅ በመሆኑ ለሽያጭ የተዘጋጀዉ ነዳጅ ለቃጠሎው መከሰትና መባባስ ምክንያት ሆኗል።
ከስድስት ወር ልጇ ጋር ህይወቷ ያለፈችዉ እናት በእሳት አደጋዉ ከተቃጠሉት የንግድ ሱቆች ዉስጥ በአንደኛዉ ሱቅ የንግድ ስራ ላይ የነበረች መሆኗን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል።
ነዳጅ ማከማቸትም ሆነ መሸጥ ያለበት በተፈቀደለትና የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ባሟሉ የነዳጅ መሸጫ ጣቢያዎች ዉስጥ ብቻ መከናወን ያለበት በመሆኑ በተለያዩ የንግድ ሱቆች ዉስጥ ነዳጅ ማከማቸትም ሆነ መሸጥ መሰል አደጋዎችን የሚያስከትል በመሆኑ የንግድ ፈቃድ የሚሰጡ አካላት ተገቢዉን ቁጥጥር ማድረግ ይኖርባቸዋልም ሲሉ አክለዋል።
በትግስት ላቀው
#ዳጉ_ጆርናል