ህብረት ኢንሹራንስ ባለፈው በጀት ዓመት
612 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ
ከ30 ዓመታት በፊት በአንድ ቅርንጫፍ ቢሮ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ሕብረት ኢንሹራንስ የማይቋረጥ ፈጣንና ጥራት ያለው አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ አስታውቋል።
በተጠናቀቀው የ2023/24 የበጀት ዓመት ወደ 2 ቢሊዮን ብር የተጠጋ አረቦን መሰብሰብ የቻለ ሲሆን ይህም የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪውን ከሚመሩ ሶስት ቁንጮ ኩባንያዎች አንዱ አድርጎታል ተብሏል።
በትርፋማነት ረገድ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በተለያየ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ደንበኞች 693 ሚሊዮን ብር ካሳ ከፍሎ ከግብር በፊት 612 ሚሊዮን ትርፍ ማግኘቱን የህብረት ኢንሹራንስ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ወንድወሰን ተሾመ መናገራቸውን ብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።ኩባንያው በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ለእያንዳንዱ አክሲዮን ከብር 527 በላይ የትርፍ ድርሻ ማከፋፈሉን ተናግረዋል።
አያይዘዉም ዛሬ ላይ የኩባንያው ባለአክሲዮኖች ቁጥር 714 እንደደረሰ ተናግረዉ የተፈረመ ከፒታሉ 1.5 ቢሊዮን ብር ደርሷል።
ከእዚህም ውስጥ ሙሉ በሙሉ የተከፈለ ካፒታሉ 1.1 ቢሊዮን ብር እንደሆነ የተናገሩት አቶ ወንድወሰን ጠቅላላ ሃብቱ ወደ ብር 4.5 ቢሊዮን አድጓል ሱሉ ጨምረዉ ገልፀዋል፡፡
ህብረት ኢንሹራንስ በአሁኑ ወቅት የ30ኛ አመቱን የምስረታ በአል በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚያከብር በዛሬዉ እለት በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ አስታዉቋል።
በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል