ከሰሞኑ እየተከሰተ ያለው ጉንፋን መሰል በሽታ 35 በመቶ አር ኤስ ቪ ቫይረስ መሆኑ ተነገረ
ባለፉት ሁለት ወራት መስከረምና ጥቅምት 2017 ዓመተ ምህረት ከሁሉም የቅኝት ጣቢያዎች የተሰበሰቡ ናሙናዎች እንደሚያሳዩት በኢትዮጲያ የተከሰተው ጉንፍን መሰል በሽታ 35 በመቶው አር ኤስ ቪ የተባለ ቫይረስ መሆኑን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት አስታዉቋል።ኢኒስቲትዩቱ በዚህ ዙሪያ ባወጣው መረጃ መሰረት የጉንፋን በሽታ በተፈጥሮ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች ማለትም አፍንጫን፣ ጉሮሮን እና የአየር መተላለፊያ ባንቧን የሚያጠቃ ተላላፊ ሕመም ነዉ።
በርካታ ቫይረሶች ለጉንፋን መከሰት ምክንያት ቢሆኑም በጣም የተለመዱት ግን ሪኖ ቫይረስ ፣ኮሮና ቫይረስ፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ፓራ ኢንፍሉዌንዛ፣ አር ኤስ ቪ(RSV) ቫይረሶች ሲሆኑ ሪኖ ቫይረስ ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳልም ብላል። በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የመተንፈሻ አካላት ቫይረስ በሽታዎች ቅኝትና ምላሽ ክፍል በክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች በተመረጡ የጤና ተቋማት የቅኝት ስራውን በመደበኛነት ላለፉት 15 አመታት እየሰራ ይገኛል።
በዚህም መሰረት ባለፉት ሁለት ወራት መስከረምና ጥቅምት 2017 ከሁሉም የቅኝት ጣቢያዎች የተሰበሰቡ ናሙናዎች መካከል 35በመቶ አር ኤስ ቪ፣ 6.2በመቶ ኢንፍሉዌንዛ፣ እንዲሁም 2 በመቶ የኮረና ቫይረስ ተጠቂ መሆናቸው ተረጋግጧል። የአር ኤስ ቪ (RSV) ቫይረስ ተጠቂዎች ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ወቅት ከሚከሰተው መጠን ከፍ ያለ ሲሆን ቫይረሱ ከተገኘባቸው ህሙማን መካከል 88 ነጥብ 5 በመቶ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ5 አመት በታች የሆኑ ህጻናት ናቸው፡፡
ይህ ቫይረስ ደረቅና ነፋሻማ የአየር ፀባይ (ወቅት) ቫይረሶች በተሻለ ሁኔታ እንዲሰራጭ ስለሚያግዝ እና የአፍንጫ የውስጠኛው ስስ ሽፋን (ሙከስ መምብሬን) ስለሚደርቅ የጉንፋን ሕመም እና ተላላፊነቱ ይጨምራል፡፡ ሳል፣ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ ጉሮሮን መከርከር፣ ማስነጠስ፣ የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት፣ አይን ማሳከክ እና መቅላት፣ ማስታወክ፣ ከፍተኛ ድካም፣ ብርድ ብርድ ማለት፣የትንፋሽ ማጠር እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ምልክቶች ናቸዉ።
ይህ የጉንፋን መሰል በሽታ ሁሉንም ሰው የሚያጠቃ እና በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ሲሆን በቫይረሱ የተጠቃ ግለሰብ በሚያስልበት እና በሚያስነጥስበት ጊዜ ከሚወጡ ጠብታዎች ጋር በሚኖር ቀጥተኛ ንክኪ፣ እንዲሁም ቫይረሱ ያረፈበትን ቁሳቁስ ወይም እጅ ከነኩ በኋላ አፋቸውንና አፍንጫቸውን ሲነካኩ ቫይረሱ በሚፈጠርለት ምቹ ሁኔታ ሊተላለፍ ይችላል።ለሚቀጥሉት 2 ወራት የኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ ስርጭት ሊጨምር እንደሚችል ኢኒስቲትዩቱ ቅድመ ግምቱን ሰጥቷል፡፡
በትግስት ላቀው
#ዳጉ_ጆርናል