በጢያ መካነ ቅርስ አካባቢ የሚገነባዉ ዘመናዊ ሎጅ እስከ 4 ቢሊዮን ብር በጀት እንደሚጠይቅ ተነገረ
ከ12ኛዉ እስከ 14ኛዉ ክፍለ ዘመን እንደተተከለ የሚነግርለት እና ከአዲስአበባ በ84 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሚገኘዉ የጢያ ትክል ድንጋይ በመደመር ትዉልድ መፅሐፍ ሽያጭ ገቢ በቦታዉ ላይ ዘመናዊ ሎጅ ለመገንባት ከሁለት አመት ገደማ በፊት የመሠረት ድንጋይ መጣሉ ይታወሳል፡፡ ለትግበራ አመቺ የሆነ ዲዛይን እና ዕቅድ ቢያልቅም ወደ ግንባታ እንዳልተገባ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ቡርክታዊት ፀጋዬ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
ቦታዉ ላይ ዲዛይኑ በርካታ ነገሮችን ያካተተ ሲሆን ባህላዊ ሬስቱራንትና ሎጅ ዋነኛዎቹ ሲሆኑ ቱሪስቶች ወደ መካነ ቅርሱ በሚመጡበት ወቅት ምቾት ተሰምቷቸዉ እዛዉ እንዲቆዩ የሚረዳቸዉ ነገሮች በሙሉ በዲዛይኑ ላይ መካተታቸዉ ተገልጿል ።
ወደ ግንባታ መግባት ያልተቻለዉ ከመደመር ትዉልድ መፅሀፍ ሽያጭ የሚጠበቀዉ ገቢ ተጠናቆ ባለመግባቱና ከሀብት አሰባሰብ ጋር ተያይዞ ጉድለቶች በመኖራቸዉ መሆኑን ገልፀዉ አሁን ላይ ግን ክልሉ ፣ዞኑ ፣ወረዳዉን ጨምሮ ትኩረት ሰጥቶ እየሰሩ መሆናቸዉንና ጨረታ ለማዉጣት ዝግጅት ላይ መሆናቸዉን ገልፀዋል ።
ለግንባታዉ ከ3.5 እስከ 4 ቢሊዮን በጀት እንደሚፈጅ የሚጠበቅ ሲሆን በዕቅዱ መሠረት ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 3 ተከታታይ አመታት ዉስጥ ግንባታዉ እንደሚያልቅ ይጠበቃል።የጢያ መካነ ቅርስ ተከልሎና ለእይታ ምቹ ሆኖ ቢቀመጥም ቱሪስቱ እዛ አከባቢ ቆይቶ ተገቢዉን ገቢ ከማግኘት አንፃር ሰፊ ችግር እንዳለ ተገልጿል ።
ግንባታዉ ሲጠናቀቅ የቱሪስቱ ቁጥር ስለሚጨምር የገቢ መጠኑም በዛዉ ልክ እንደሚጨምር ይጠበቃል።አከባቢዉ ላይ ያለዉም ኢኮኖሚ ከማነቋቋት በተጨማሪ እስከ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ጫፍ ድረስ ያለዉን ኢኮኖሚ ያነቃቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ወ/ሮ ቡርክታዊት ፀጋዬ ጨምረዉ ገልፀዋል።
በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል