በሎስ አንጀለስ በሰደድ እሳት የተነሳ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ
ከ10 ሄክታር መሬት በላይ በሰዓታት ውስጥ በሰደድ እሳት የወደመ ሲሆን ከ2,900 ሄክታር የሚበልጥ አካባቢ በእሳት በመያያዙ ሎስ አንጀለስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇለች። የእሳት አደጋ መከላከያ አዛዥ ክሪስቲን ክራውሊ ከ30,000 በላይ ሰዎች አካባቢያቸውን እንዲለቁ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው በመግለፅ 13,000 ህንጻዎች ስጋት ላይ ናቸው ብለዋል። በፓስፊክ ፓሊሳዴስ አካባቢ ያሉ ቤቶች በእሳት ሲቃጠሉ እና ነዋሪዎች እሳቱን ለመሸሽ መኪናቸውን እንኳን መጠቀም ሳያስፈልጋቸው ጥለው ሲወጡ የሚያሳይ ምስል በስፋት ተሰራጭቷል።
እሳቱ የተነሳው ማክሰኞ ከቀኑ 10፡30 አካባቢ ሲሆን በሰአት 80 ኪሜ ፍጥነት ያለው ንፋስ እና ደረቃማ ሁኔታ ተስተውሏል። የሎስ አንጀለስ የእሳት አደጋ መከላከያ አዛዥ አንቶኒ ማርሮን የፓሲፊክ ፓሊሳድስ “ከአደጋ አልወጣም” ብለዋል ። በካሊፎርኒያ ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አደጋው ሊስፋፋ ይችላል በሚል ማስጠንቀቂያ ስር ናቸው፣ ይህም ማለት ከፍተኛ የእሳት አደጋ እንደሚኖር ያሳያል።
በሎስ አንጀለስ ውስጥ ከ46 ሺ በላይ መኖሪያ እና ንግድ ቤቶች የኤሌክትሪክ ኃይል አጥተዋል። ባለሥልጣናቱ አስቀድመው እንዳስጠነቀቁት ነፋሱ ሌሊቱን ሙሉ ሊጨምር የሚችል በመሆኑ የኤሌክትሪክ መስመሮችን ሊያወድም እንደሚቻል ተናግረዋል ። ሌሎች 8,000 ደንበኞች በአጎራባች ሳን በርናርዲኖ የኃይል አቅርቦት ተቋርጦባቸዋል። የካሊፎርኒያ ገዥ ጋቪን ኒውሶም እንዳሉት "ጥቂት ሳይሆን ብዙ ግንባታዎች" ወድመዋል ያሉ ሲሆን ትክክለኛውን የውድመት መጠን ግን ከመግለፅ ተቆጥበዋል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል