ከ340 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ማርህይወት የእናቶችና ህፃናት ልዩ የህክምና ማዕከል በይፋ ተመረቀ
ማርህይወት የእናቶች እና ህጻናት ልዩ የህከምና ማዕከል አገልግሎቱን በተገቢው መንገድ ለመስጠት እንዲያስችለው እራሱ ባስገነባው ባለ 5 ወለል ሀንጻ ላይ እንዲሁም ልምድ ባካበቱ ከ10 በላይ ስፔሻሊስት እና ሰብ ስፔሻሊስት ሃኪሞችን በመያዝ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የምርቃት መርሐግብሩን አስመልክቶ የማርህይወት የእናቶች እና ህጻናት ልዩ የህከምና ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጅ ባለቤት አቶ ሀብታሙ አሰፋ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልጸዋል።
ከፍተኛ የህክምና ባለሞያዎችን ጨምሮ በቋሚና በጊዜያዊነት ከ90 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል የፈጠረው ማርህይወት የእናቶች እና ህጻናት ልዩ የህከምና ማዕከል በውስጡ እጅግ ዘመናዊ የቀዶ ሀክምና ክፍሎች፣ እናቶች እና ህጻናት ተኝተው የሚታከሙበት መደበኛ እና ቪአይፒ ክፍሎች፣ አርተፊሻል መተንፈሻ ማሽን ፣ የጨቅላ ህጻናት ጽኑ ህሙማን ክፍልን ጨምሮ እጅግ ዘመናዊ አልትራሳውንድ ፣ ኤክስ ኤሪ እና የተሟላ የላቦራቶሪ ክፍሎችን የያዘ ማዕከል እንደሆነደግሞ የገለጹት የማዕከሉ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዶክተር ዳግማዊ እዝራ ተናግረዋል።
ስራ ከጀመረ ከጥቅምት 2017ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ከ 750 በላይ ታካሚዎችን ያስተናገደው የህክምና ማዕከሉ በቀጣይ አንድ አመት ውስጥ የተራቀቀ የመካንነት ህክምና እና ላፓራስኮፒ ወይም በካሜራ የታገዙ ቀዶ ህክምናዎችን ለመጀመር የታቀደ ሲሆን ሙሉ በሙሉ የተፈጥሮ ጸሀይ ኢነርጂን በመጠቀም ከአየር ብክለት የጸዳ 24 ሰዓት የማይቋረጥ የኤሌክትሪክ ሀይል ያለው ሲሆን በተመሳሳይ ደግሞ ራሱ በስቆፈረው የከርሰ ምድር ውሃ ንጽህናው የተጠበቀ ተቋም ለመፍጠር ችሏል።
በምረቃው መርሐግብር ላይ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎ ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል