በኦንላይን ትኬት በመቁረጥ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት መሰጠት ሊጀመር ነው
የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አ.ማ ከየካቲት 2017ዓ.ም ጀምሮ በኦንላይን ትኬት በመቁረጥ የህዝብ መንገደኞች ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡
የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ(ኢ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ÷ አክሲዮን ማህበሩ ከየካቲት 2017 ጀምሮ በኦንላይን ቦታ በማስያዝ የህዝብ መንገደኞች ትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚጀምር ገልፀዋል።
ጥራት ያለዉ እና ቀልጣፋ የጉዞ አገልግሎት ለመስጠት ፣ ትክክለኛ የመንገደኛ መረጃን ለማረጋገጥ እንዲሁም ከችግር የጸዳ ጉዞን ለማመቻቸት አስፈላጊ በመሆኑ ለሁሉም የሀገር ውስጥ ተሳፋሪዎች ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) በመጠቀም ኦንላይን ቦታ ለመያዝም ሆነ ለመጓዝ መስፈርት መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
#ዳጉ_ጆርናል