በዛሬው ዕለት በመላው የትግራይ ከተሞች ሊባል በሚችል ደረጀ ሰልፎች እየተደረጉ ነው
ስልፎቹ ገሚሶቹ ሰሞኑን "የትግራይ ሰራዊት የበላይ አመራሮች" ያስተላለፉትን ውሳኔ የሚቃወሙ ገሚሶቹ ደግሞ የሚደግፉ መሆናቸው ዳጉ ጆርናል ከተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ለመመልከት ችሏል።
መቐለ፣ተምቤን ዓብይ ዓዲ፣ ጣንቋ ምልሽ፣ ኮረም፣ ዓዲ ግራት፣ አኽሱም፣ ውቅሮና እንትጮ ሰላማዊ ሰልፍ ከተደረገባቸው ከተሞች መካከል ይጠቀሳሉ።
በሰልፎቹም በአንድ በኩል ከፍተኛ የጦር አመራሮቹ የወሰኑት ውሳኔ እንዲተገበርና ጊዝያዊ አስተዳደሩ እንደ አዲስ እንዲዋቀር የተጠየቀ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የጦር አመራሮቹ ውሳኔን የሚቃወም ብሎም ትግራይ ላይ ዳግም ጦርነት እንዲነሳ አንፈልግም የሚሉ ድምፆች ተሰምተዋል።
በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል