የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ የነዋሪነት አገልግሎት የወረዳ ጽ/ቤት አመራር በ10ሺ ብር ተደራድረው የዲጂታል ምዝገባ ሲያከናውኑ በቁጥጥር ስር ዋሉ
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በደረሰው የተገልጋይ ጥቆማ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ አያለው እንዲሁም የነዋሪ መርጃ፣ ህትመት ስርጭት እና ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ መንግስቱ እጅጉ በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
ተከሳሾቹ በጋራ በመመሳጠር ላልተገባ ሰው አገልግሎትን በገንዘብ ለመሸጥ በ10ሺ ብር ተደራድረው የዲጂታል ምዝገባ በማከናወን ላይ ሳሉ በተደረገው ክትትል እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
የተቋሙ የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ክፍል ከፖሊስ ጋር በመተባበር ላለፉት ሶስት የስራ ቀናት ክትትል ሲያደርግ በመቆየት ተጠርጣሪዎቹ የካቲት 17 ቀን በጽ/ቤቱ ውስጥ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል። ተቋሙ በክትትሉ የተደራጁ የድምፅ ቅጂ እና ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለፖሊስ አስረክቧል።
ተቋሙ ከህገ-ወጥነት ለመከላከል የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና የስራ ክፍል የመረጃ አቅምን እያጠናከረ ያለና የዲጂታል አገልግሎቱም ኦዲት የሚደረግበት ስርዓት በመዘርጋት ከህገ-ወጥ ደላሎች እና አገልግሎትን በገንዘብ ከሚሸጡ ሰዎች ራሳቸውን መጠበቅ እንደሚገባቸው አቶ ዮናስ ዓለማየሁ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል