ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ውጪ ከ100 በላይ ሰዎችን ቀጥረዉ ወርቅ በማዉጣት ሲያሰሩ የነበሩ 16 ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ
በኢሊባቡር ዞን ነዲ ወረዳ ጀዊ ቀበሌ ውስጥ ከሚመለከተው አካል ፍቃድ እና እውቅና ውጪ በማዕድን ቁፋሮ ላይ የተሰማሩ 16 ግለሰቦች በእስራት ሲቀጡ ለቁፋሮ የተጠቀሙበት ቁሳቁስ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን መወሰኑን የኢሊባቡር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታዉቋል።
የኢሊባቡር ዞን ፖሊስ መምሪያ የኮምኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ለማ ቦይዶ ለብስራት እንደተናገሩት አስራ ስድስቱ ግለሰቦች ካለማንም ፍቃድ እና እውቅና ውጪ ራሳቸውን አደራጅተው በስሮቻቸው ከ መቶ ሰዎች በላይ ቀጥረው በህገወጥ መንገድ የወርቅ ማዕድን ሲያወጡ በመገኘታቸው በእስራት ሊቀጡ ችለዋል።
ፖሊስ በደረሰው መረጃ መሠረት አስራ ስድስቱን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር በማዋል ከአቃቤ ህግ ጋር በመሆን የምርመራ መዝገባቸውን በማጣራት አቃቤ ህግ የኦሮሚያ ክልል የማዕድን ውጤቶችን ለማስተዳደር እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ድንጋጌ ቁጥር 223/2012 አንቀፅ 8 መሠረት ክስ የመሠረተ መሆኑን ገልፀዋል።
በአቃቤ ህግ የተመሠረተውን ክስ ሲከታተል የነበረው የነዲ ወረዳ ፍርድ ቤትም አስራ ስድስቱ ግለሰቦች ጥፋተኛ በማለት በ አራት ወር ቀላል እስራት የተቀጡ ሲሆን በቁፋሮ የተገኘ 131 ኪሎግራም ወርቅ እና 153 ሺህ ጥሬ ገንዘብ እንዲሁም 3 ጄነሬተር ፣ 16 ዲጂኖ ፣15 የወርቅ ማንጠሪያ ገበቴ እና 3 የወርቅ ሚዛን ለመንግስት ገቢ እንዲሆን መወሰኑን ምክትል ኢኒስፔክተር ለማ ቦይዶ ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል።
በሰመኃር አለባቸዉ
#ዳጉ_ጆርናል