መረጃ‼️
ደቡብ ወሎ_ደሴ
በትናንትናው እለት በከተማዋ በሚገኜው የ'ወሎ-ባሕል-አምባ' አዳራሽ አንድ ትልቅ ስብሰባ ተከናውኗል። ስብሰባው ከዞን ፣ እና ወረዳ ሚልሻ ጽ/ቤት ዘርፍ ኃላፊዎችን ያካተተ ሲሆን ፤ በክልሉ የሚሊሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ልጃለም ፣ በደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አሳመን ፣ እና በደሴ ከተማ ከቲባ ኃላፊ በሆኑት አቶ ሳሙኤል ጥምረት የተመራ ነበር።
ከአማራ ልዩ ኃይልነት ወደ መደበኛ ፓሊስነት የገቡ የቀድሞው የልዩ ኃይሉ አባላት ፣ እና በዞኑ ውስጥ ያሉ ወረዳዎችን የጸጥታ፣ እና ሚሊሻ ዘርፍ ቢሮዎችን በኃላፊነት የሚመሩ የብልጽግና ካድሬዎች ተሳታፊዎች የነበሩ ሲሆን ፤ የመድረኩ አላማም የልዩ ኃይል አባላቱን (ወደ ፖሊስነት የገቡ) በጥቅም በመደለል (አደራጅተን ቤት መስሪያ መሬት እንሰጣለን) እና በማሳመን ፤ ከየወረዳዎቹ ከሚገኙ ታጣቂ ሚሊሻዎች ጋር አቀናጂቶ በሰላም አስከባሪ ስም ወደ ወንድሞቻቼው (ፋኖ) መላክ ፣ እና እርስበርስ ማገዳደል ሲሆን ፤ መድረኩ ፍሪያማ ሳይሆን መቅረቱ ታውቋል። በተለይ ከቀድሞዎቹ የአማራ ልዩ ኃይል አባላቱ በኩል፣ ያልተጠበቀ እና ከፍተኛ የሆነ ቅሬታ ተሰንዝሯል።
ብአዴን ልዩ ኃይሉን ከበተነ በኃላ ጭንቀት ውስጥ መግባቱ ግልጽ ሲሆን ፤ ይህንን ጭንቀቱን ለማቃለል "ሰላም አስከባሪ" የሚል ቡድን ለማዋቀር ወስኖ ወደ ስራ የገባ ሲሆን፤ በቅርቡ በክልል ም/ቤት ደረጃ የተወሰነ ሲሆን ፥ መዋቅሩም ከክልል እስከ ቀበሌ በየደረጃው የሚወርድ ሆኖ ፤ ያፈረሰውን የአማራ ልዩ ኃይልን ቦታ ተክቶ እንዲንቀሳቀስ የታለመለት ኃይል ሲሆን ፤ "የክልል ሰላም-አስከባሪ ዘርፍ" በመባል የሚጠራ መሆኑ ታውቋል።
//መረጃው ከምንጮቻችን እንደደረሰንን የቀረበ ነው።//