ዘሪሁን ገሠሠ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Политика


በመረጃ እንቀራረብ! በመረጃ እንተሳሰር!

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Политика
Статистика
Фильтр публикаций


ፋኖ እና የአማራ ብሄርተኝነት ምንና ምን ናቸው?

// በሀይሉ ቢታኒያ//

ፋኖ እና የአማራ ብሄርተኝነት አንድና ያው ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ፋኖ ከመዋቅሮች (structures) መካከል አንዱ ነው፡፡ የአማራ ብሄርተኝነት ከሁሉም መዋቅሮች በላይ የሆነ ዣንጥላ መዋቅር (overarching structure) ነው፡፡ “ርእሰ መዋቅር” እንበለው፡፡ በአማራ ብሄርተኝነት ርእዮት የተቃኙ የሚዲያ ተቋማት፣ በአማራ ብሄርተኝነት ርእዮት የተቃኙ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ የጥናትና ምርምር ተቋማት፣ የፖለቲካ ድርጅት/ቶች፣ እንዲሁም በአማራ ብሄርተኝነት ርእዮት የተቃኘ አርበኛ ሰራዊት (ፋኖ) ያስፈልገናል፡፡ ይሁን እንጅ ከእነዚህ ተቋማት መካከል አንዱም ብሄርተኝነቱን አይተካም፡፡ ከብሄርተኝኑ ጋር እኩል ሊሆንም አይችልም፡፡ ብሄርተኝነቱ እስከተጠናከረ ድረስ እንድ ተቋም በተለያየ መንገድ ችግር ውስጥ ቢገባ ራሱን አርሞ ይድናል፡፡ ሳይሆን ቀርቶ ከፈረሰም በሌላ ይተካል፡፡

ስለሆነም የአማራ ብሄርተኞች የሁልጊዜም ታማኝነታችን ለብሄርተኝነቱ፣ ከእሱ ቀጥሎ ለድርጅቶች/ተቋማት መሆን ይገባዋል፡፡ ጠንካራ መሪዎችን የሚፈጥራቸው በጠራ ርእዮት የሚመራ ድርጅት ነው፡፡ የቻይናው አብዮታዊ መሪ ማኦ ሲ ቱንግ ብቻውን ኮምኒስት ፓርቲውን አልገነባውም፡፡ ከሌሎች ጓዶቹ ጋር ሆኖ ነው፡፡ ፓርቲው የእሱ የእጅ ሥራ አይደለም፡፡ በጋራ አመራር የተገነባ ነው፡፡ ማኦን ማኦ ያደረገው ፓርቲው ነው፡፡ ማኦ ከፓርቲው ቢወጣ ማንም እዚህ ግባ የማይለው ተራ ግለሰብ ሆኖ በቀረ ነበር፡፡

ስለዚህ በሶስዮሎጂስቶቹ አባባል methodological collectivist እንሁን፡፡ ዋነኛው ታማኝነታችን ለህዝባችን (ይኸውም ለብሄርተኝነቱ) ይሁን፡፡ ከእሱ ቀጥሎ በብሄርተኝነት ርእዮት ለተገነቡት ድርጅቶች ይሁን፡፡ ግለሰብ መሪዎችን ማክበር ያለብን በመዋቅሩ/በድርጅቱ አሰራር መሰረት ነው፡፡ እሱን ተከትለን እናክብራቸው፡፡ ከዚህ ውጪ ግለሰብ ማምለክ ወይም ግለሰብን ማዋረድና ሲረግሙ መዋል ግን ከብሄርተኛ የሚጠበቅ አይደለም፡፡

የአማራ ብሄርተኝነት ይለምልም!!!


ደራሲ አዜብ ወርቁ ዛሬ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሏ ተሰምቷል!

አዜብ ሰሞኑን በጫካ ፕሮጀክት ምክንያት ስለሚነሱ ነዋሪዎች ''ልማት የሰውን ልጅ ሲያፈርስ አየሁ'' በሚል ርዕስ  አንድ ፅሁፍ በማህበራዊ ሚዲያዎች ካጋራች በኋላ ጽሁፉ በስፋት መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። በኋላም ከማህበራዊ ገጿ ጽሁፉን ማንሳቷን ማስታወቋም አይዘነጋም።

ታዲያ! ''ትችት'' የሚባል ነገር ፈፅሞ እንዲሰነዘርባቸው የማይሹት ፍፁም አምባገነኖቹ ፣ ግለሰቧን አፍነው ወደሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወስደው እንዳሰሯት ቤተሰቦቿን ዋቢ አድርጎ አንከር ሚዲያ ዘግቧል።

የጉድ ሀገር!


ትግሉ ጠንካራ ውስጣዊ የፋይናንስ ድጋፍ መሠረት ሊገነባ ይገባል!

IMF ለነአብይ ብድርና ድጋፍ ሲያደርግ አመታትን የፈጀ ድርድር አድርጎ ''የብር የመግዛት አቅምን ማዳከምን'' ጨምሮ በርካታ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሟሉ ብሎም ፣ እጅ ጠምዝዘው ከእነሱ ፍላጎትና ጥቅም አንፃር የተቀኘ የኢኮኖሚ ስርአት እንዲገነባ በማድረግ ነው! ያው ምዕራባውያን ድህነትህን ተጠቅመው በእጅ አዙር ባሪያ እንደሚያደርጉህ የሚታመን ነው!

በአማራ ህዝብና ትግል ስም ገንዘብ ሰብስበህ ለመስጠት ፣ ቅድመ ሁኔታ የምታስቀምጥና ተናጠላዊና ቡድናዊ ፍላጎትህን ለማሳካት መደራደሪያ የምታደርግበት ከሆነ ከምእራባውያኑ አበዳሪዎች በምን ትለያለህ ? እነአብይንስ ስለምን ትተቻለህ ?

እንደው ሀተታውን ልተወውና ... የአማራ ህዝብ የህልውናና የነፃነት ተጋድሎ መደገፍና የፋይናንስ ምንጩ መሠረት መሆን ያለበት ፣ በራሱ ሀገር ቤት ባለው ህዝቡ ነው!

ይህን ውስጣዊ የድጋፍ መሠረት መጣል የምትችለው ደግሞ ፣ በጠራ አስተሳሰብና አላማ ላይ ተመርኩዞ የተገነባ የጋራ ተቋማዊ መንገድና አደረጃጀት መስራት ስትችል ብቻ ነው!

በአማራ ኮዝ ላይ ለመታገል ወጥተህ ፣ ርእዮተ-አለማዊና የግብ ልዩነት ሳይኖርህ ፣ ህብረትና አንድነትን ለማምጣት ብሎም የተማከለ ተቋማዊ አስተዳደር ለመገንባት አዳጋች ከሆነብህ ፣ እመነኝ! አንድም እራስህን ፈትሽ ሁለትም ራስህ በፈጠርክላቸው ክፍተት ተጠቅመው ጠላቶችህ ከውስጥ ወደውጭም ፣ ከውጭ ወደውስጥም እየሸረሸሩህ መሆናቸውን አበክረህ ተረዳ!

ተቦርቡረህ ላለመውደቅና ላለመሰባበር ያለህ ብቸኛ አማራጭ ደግሞ ፣ ግለኝነትን (ቡድንተኝነትን) ነቅለህ ፣ በጠራ አስተሳሰብና አላማ ላይ ተመርኩዞ የተገነባ የጋራ ተቋማዊ መንገድ ገንብተህ ተጓዝ!

ከዚያ ውጭ የፈለገ የቀጠናውን ግዙፍ ሰራዊት በየፊናህ ብትገነባ ፣ እርስበርስህ ከመናከስ ፣ በገዛ ልምጭህ ከመገረፍ ፣ የማንም ሀሳብና ፍላጎት መጫኛ ከመሆን ብሎም አይደለም ህዝብን ራስህንም ለመታደግ ከማትችልበት ማጥ ውስጥ መዘፈቅህ ሳይታለም የተፈታ ነው!


ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ ፤ እንኳን ለ1499ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰዐወ) የልደት በዓል (መውሊድ) በሠላም አደረሳችሁ! አደረሠን!


የምለው ይሄን ነው!

ከህዝባችሁ ጎን ቆማችሁ ግፈኞችን በመሞገታችሁና በማንነታችሁ ምክንያት እየታደናችሁ ፣ ለአንባገነናዊ እስር ተዳርጋችሁ ለምትገኙ ወንድም እህቶቼ ፤

ገዢዎች ከአመት አመት ሲሻገሩ እነዚያ በደም አፋሳሽ ጦርነትና በዘር ፍጅት ሰለባ ሆነው መሻገር ያቃታቸው የሚሊየኖች ወንድም እህቶቻችንን ሀዘን የተሸከማችሁ እናቶች፤

አመት በመጣ ቁጥር ስርአት ሰራሽ የኑሮ ጫናንና ጉስቁልናን መቋቋም ተስኗችሁ '' ልጆቼን ምን ላብላ? እንዴት ላስተምር ?'' እያላችሁ የምትብሰለሰሉ የመንግስት ሰራተኞች፤

''ፋሺዝምን የሚሸከም ጫንቃ የለንም'' ብላችሁ ባመናችሁበት መንገድ ተጋድሎ እያደረጋችሁ ላላችሁ ወገኖቼ ፤

በሀገራችሁ ዩኒቨርስቲዎች የመማር እድልን ፖሊሲ-መር በሆነ መልኩ ተነፍጋችሁ በስነልቦናዊ መቃወስ ውስጥ የምትገኙና ''ለመንግሥት ፖሊሲ መር ጦርነት'' የታጫችሁ በሚሊየን የምትቆጠሩ ወጣት የሀገር ተረካቢ ተማሪዎች፤

በሀገራችሁ በሰላም የመኖርን እድል ተነፍጋችሁ ለስደት የተዳረጋችሁ ወገኖቻችን ፣

በስርአት ሰራሽ ቀውስ ማጀታችሁ ለተፈታ ፣ ልጆቻችሁ ለተበተኑ ፣ ሀዘን ለተሸከማችሁ ፣ ተስፋ መቁረጥ ጥላውን ላጠላባችሁ ፣ ወላጆቻችሁንና ወዳጆቻችሁን ለተነጠቃችሁ ፣ ወጥቶ መግባት ብርቅ ለሆነባችሁ ፣ ህይወትን ብቻ ይዞ በሰቀቀን ውስጥ ከአመት አመት መሻገርን በመናፈቅ ላይ ላላችሁ ፣ .....ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ በሙሉ ፤

አዲሱ አመት ምኞታችሁ እውን የሚሆንበት ፣ ሀዘናችሁ በደስታ የሚቀየርበት ፣ እንባችሁ የሚታበስበት ፣ ከጦርነት ሰቀቀን የምትላቀቁበት ፣ ....ብሩህ አመት ይሆንላችሁ ዘንድ ልባዊ ምኞቴን እገልፃለሁ!

🌼🌼🌼መልካም አዲስ አመት!🌼🌼🌼


አፋኞቹ ደሜንም አስረውታል!

ከሰሞኑ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብቱን ተጠቅሞ በማህበራዊ ሚዲያ የሚያነሳቸው ሀሳቦችን ተመርኩዘው ፣ አንድ በጎ ጎን ሳይኖራቸው ''አትተቹን!'' ባዮቹ አምባገነኖች ''እናስረሃለን!'' እያሉ በስልክና በሌሎች መንገዶች ሲደነፉበት እንደነበር አጫውቶኝ ነበር።

ይኸው እንደፎከሩት ብርቱው ወንድማችን ጠበቃና የህግ አማካሪ እንዲሁም መምህር ደመወዝ ካሴን በትናንትናው እለት ማሰራቸውን ሰምተናል!

ለአፈናና ለእገታ ተግተው የሚሠሩትን ያህል ፣ የህዝብን ሁለንተናዊ ጥያቄዎች ለመመለስ በርትተው ቢሰሩኮ የሚሠነዘርባቸውንም ትችትና አስተያየት መቀነስ በቻሉ ነበር። ፋሺዝም አስከፊ የአስተሳሰብ ደዌ ነው!

እኔ ግን እላችኃለሁ! የግፉን መስፈሪያ ሞልቶ እስከሚፈስ በሰፈራችሁት ቁጥር ፣ የቂምና የበቀል እቁብ እየጣላችሁ መሆኑን መገንዘብ ብልህነት ነው!

ወንድማችን ደመወዝን ጨምሮ በየማጎሪያው ያገታችኃቸው ወገኖቻችንን በአስቸኳይ ከመፍታት የምታተርፉት እናንተው ናችሁና ፍቷቸው!


ከወንጀሉም በላይ ....!

ጦርነት አማራጭ ሲጠፋ የሚገባበት አውዳሚና ጥቁር ጠባሳን ጥሎ የሚያልፍ ጉዳይ መሆኑ ፈፅሞ አከራካሪ አይሆንም። ጦርነት አንድን ፖለቲካዊ አላማና ግብ ለማሳካት በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ተዋጊ ኃይሎች መካከል ይደረግ እንጂ ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ የሚያስከትለው የጎንዮሽ ጉዳት/collateral damage ከተዋጊ ሀይሎቹ ባሻገር ፥ መጠኑና አይነቱ ቢለያይም ጦርነቱ በሚካሄድበት አካባቢ ያሉ ያልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎችን ሰለባ እንደሚያደርግ የሚታመን ነው።

በጦርነት ውስጥ ጦርነቱ በፈጠረው አመቺ ሁኔታ የዘረፋ ፣ የእገታና የግድያ ወንጀሎች እንደሚበራከቱም በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል። አለማቀፋዊ የጦር ስምምነቶች ለሲቪሎች ጥበቃና ከለላ እንዲደረግ ብሎም ተዋጊ አካላትም ይህን ህግ እንዲያከብሩ የሚያስገድዱ ቢሆንም ፣ የሚደርሱትን የጦር ወንጀሎች መቆጣጠር ወይም መግታት ግን ሲቻላቸው አይስተዋልም።

እዚህ ጋር በሁለት ተዋጊዎች መካከል በሚደረግ ጦርነት ውስጥ ፣ አንደኛው አካል የሌላኛውን ስም ለማጉደፍና ከህብረተሰቡ ለመነጠል ሲል ሆነ ብሎ የተለያዩ ወንጀሎችን በመፈፀም አለያም በማስፈፀም ይህ ካልሆነም ጦርነቱን እንደመልካም አጋጣሚ ተጠቅመው ባልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የተደራጀ ወንጀል የሚፈፅሙ ጥገኛ ሀይሎችን ተግባር ባለቤቱን በመቀየር ፥ የፖለቲካ ቁማር ለመጫወት የሚደረግ አፀያፊ ተግባር ደግሞ በእጅጉ ያሳዝናል።

ወንጀል በማንኛውም አካል ይፈፀም መወገዝና ተጠያቂነትን ማስከተል ያለበት እኩይ ተግባር ነው። ሆኖም ወንጀልን የፖለቲካ ቁማር መቆመሪያ ማድረግ ግን የጭካኔ ሁሉ ጭካኔ ነው። ለተጎጅዎች ትክክለኛ ፍትህ እንዳይሰፍን የሚያደርግ ሀላፊነት የጎደለው ተግባርም ነው።

በአማራ ክልል የእገታና የዘረፋ ወንጀሎች ከጊዜ ወደጊዜ እየተበራከቱ መምጣታቸው አሳሳቢ ሆኖ ከመምጣቱም ባሻገር እነዚህ ወንጀሎችን ከመቆጣጠርና ትክክለኛ ፍትህ እንዲሰፍን ከመስራት ይልቅ '' ፅንፈኛው ኃይል ፣ ጃውሳው ፣ ፋኖው ፣ .....'' የሚል የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በመክፈት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት መትጋት ከወንጀሉም በላይ አሳዛኝ የሆነ ርካሽ ተግባር ነው።

ለአብነት በውጊያ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች የሚገኙ ባንኮችን መደበኛ ስራቸውን እንዲቀጥሉና ህብረተሰቡን እንዲያገለግሉ የሚጠብቅ ኃይል '' ህፃን አግቶ ገንዘብ ተቀበለ ወይም ገደለ'' የሚል ፕሮፓጋንዳ ቢሰራበት ውሃ የሚያነሳ ይሆናልን ? '' ቢፈልግ የሚታገልለትን ህዝብ አግቶ ገንዘብ ከመቀበል ትህነግ ሲያደርገው እንደነበረው የየባንኮቹን ረብጣ ገንዘብ እየወሰደ ለአላማው ማስፈፀሚያ አያደርግም ነበር ወይ ?'' የሚል ተጠይቅ አያስነሳምንስ ? ይህ አይነቱ ተራ ፕሮፓጋንዳ ለተጎጂዎች ፍትህ ከማስፈን ይልቅ በቁስላቸው ላይ እንጨት መስደድ አይሆንምን ?

እኔ ግን እላለሁ ፣ ፋኖም በስሙ የሚነግዱና አመቸን ብለው ዘረፋና ውንብድና የሚፈፅሙ አካላትን አምርሮ ይታገል ፣ ውስጡንም ለመሰል ስም ማጠልሸት አመቺ ሁኔታ የሚፈጥሩ ስንጥቆችን ይድፈን ፣ ብሎም ለሚሰነዘርበት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻም በቂና የህብረተሰቡን ብዥታ የሚያጠራ መረጃን በወቅቱ ተደራሽ ያድርግ።

የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ተቀዳሚ ሀላፊነት ያለበት ''መንግስት ነኝ'' ባዩ አካልም ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚያደርገውን ተራ ፕሮፓጋንዳ አቁሞ ፣ ከራሱ የፀጥታ መዋቅር ጀምሮ በህብረተሰቡ ውስጥ ሁኔታዎችን እንደመልካም አጋጣሚ ተጠቅመው መሰል ውንብድናና እገታ የሚፈፅሙ ሀይሎችን መቆጣጠርና ማስቆም ብሎም ለተጎጂዎች ትክክለኛ ፍትህ እንዲሰጥ የማድረግ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል እላለሁ!

'' በጎንደር ከተማ 14 የመንግስት የፀጥታ አካላትና አመራሮች ከላይ ከጠቀስኩት ወንጀል ጋር በተያያዘ ከስራ ተሰናብተው በቁጥጥር ስር ዋሉ!'' የሚለው መረጃም ትክክል ከሆነ ጥሩ ጅምር ነው! ሻወር የሚጀምረው ከራስ ነውና ...!

ፍትህ በግፍ ለተገደለችው ህፃን ኖላዊ! 😭😭😭


3 ነገሮችን በአጭሩ ለማስታወስ ያህል!

የፈረንሳይ አቢዮት መሪ የነበረው ናፖሊዮን ቦናፓርቴ > የሚል ዝነኛ አባባል አለው።

በግርድፉም > እንደማለት ነው።

ታዲያ ወደእኛ ስናመጣው ፦ ትክክለኛው አውደ ውጊያ የሚካሄድበትንና ችግሮቹ በተቋማዊነት ፣ በመርህና በደንብ ሊፈቱ የሚችሉትን መሬት ላይ ያለውን የጦር ሜዳ ከነችግሮቹ እንተወውና ፣ ሳይበሩን እንደሌላ የአውደ ውጊያ ፕላት ፎርም ብንወስደው ፣ እያንዳንዳችን አወንታዊ ሚና የሚወጣ ፣ የተናበበና በአላማ የተሰናሰነ አጋዥ የፕሮፓጋንዳና የመረጃ ክንፍ መሆን ቢያቅተን እንኳ ፥ እዚህ ሳይበር ላይ ቀምመን ወደመሬት የምናወርደውን አስከፊ የትርምስ ቫይረስ መቆጣጠርና መግታት መቻል አለብን!

ሁለተኛ ፦ ማንኛችንም ብንሆን መቆም ካለብን ከአማራ ህዝብ ትግልና የትግሉ አላማ ጎን ብቻ ነው። መራራ መስዋዕትነት እየተከፈለ ያለውም ለዚሁ ህዝባዊ ትግል ብቻና ብቻ ነው። ከዚህ ውድ ዋጋ እየተከፈለበት ካለውና የወደፊት እጣፋንታህን የሚወስን ህዝባዊ ትግል ጎን መሠለፍ ካልቻልክ ደግሞ ''ዝም'' ማለት በእጅጉ ይሻላል።

ሁላችንም ከህዝቡ ትግል በታች ነን። በትግሉ ትክክለኛ ቦይ እስከፈሰስን ድረስ አብረን እንጓዛለን። ከትግሉ መስመርና ተቋማዊ የአሰራር መርሆዎች ካፈነገጥን ተቆርጠን መጣል አለያም የእርምት እርምጃን መቀበል ግድ ይላል። ይህን ማድረግ የምንችለውም ፣ ችግሮቻችንን ሁሉ በጠንካራ ተቋማዊ አሰራር የመፍታት ልምድን አዳብረን ፣ ግለሰቦች ከትግሉ አላማና ከተቋም በታች መሆናቸውን አምነን ስንቀበል ብቻ ነው።

በመጨረሻም ፦ አክቲቭዝም አያስፈልግም እያልኩ ባይሆንም ህዝባዊ ትግሉ አሁን ላይ ፣ በአክቲቪዝም ከመመራት ደረጃ ከፍ ብሎ በሁለንተናዊ መልኩ የተገኙትንና በመገኘት ላይ ያሉትን የትግል ውጤቶች ወደድል መቀየር የሚያስችለውን 'ስትራቴጂካዊ ቦይ' ተከትሎ ከሚፈስበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።

በመሆኑም የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ 'ደፈር' ብለው ገንቢ ስትራቴጂካዊ ትችቶችንና አስተያየቶችን የሚፅፉ እጆች ብሎም የሚናገሩ አንደበቶች አብዝተው ያስፈልጉታል። እነዚህን ትችትና አስተያየቶች ለማድመጥ የተዘጋጀ ጆሮና ለመቀበል የተሰናዳ ልቦናም ሊኖረን ግድ ይላል! አለበለዚያ ነገራችን ሁሉ ''ውሀ ቢወቅጡት ፣ ....'' ይሆንና ......!

ባሻዬ! You cannot be a winner without maturity and consistency.👍

ፍትህ በግፈኞች ግዞት ታስረው የመከራ ጊዜን እያሳለፉ ለሚገኙ ወንድም እህቶቻችን!


ሀቀኛና አመክንዮአዊ የትግል ጥያቄዎቻችን ሳይመለሱ ፈፅሞ ወደኃላ የለም!

በርካታ ወንድም እህቶቼ በተለያዩ መንገዶች > የሚል ጥያቄዎችን እያቀረባችሁልኝ ነው።

እርግጥ ነው! እኔን ጨምሮ በርካታ ወንድም እህቶቼ በግፍ ታግተን ለበርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ብሎም ፣ ፣ አካላዊ ብስቁልና ተዳርገን ሁለት የግፍና የመከራ አስቸኳይ ጊዜ አዋጆችን አዋሽ አርባን (ኢትዮጵያዊው ጓንታናሞ ቤይ) ጨምሮ በተለያዩ ወህኒ ቤቶች አስከፊ ወራቶችን አሳልፈናል። አሁንም በግፈኞች ግዞት እየተሰቃዩና ፍትህ ተነፍገው የሚገኙ ወንድም እህቶቻችን እጅግ በርካቶች ናቸው።

እኔም እንደአንድ ግለሰብ በእስር ላይ እያለሁ ቤተሰብን በሞት ከማጣት ጀምሮ በርካታ ስቃዮችና ምስቅልቅሎችን ማስተናገዴ የማይካድ ነው። ይህ ሁሉ ሁኔታም እንደግለሰብ ከእስር ከወጣሁ በኃላ እየፈተነኝ መሆኑ የሚታበል ባይሆንም ፣ በህዝባችን ላይ ያለእረፍት ከተፈፀመውና በመፈፀም ላይ ካለው ጭፍጨፋና ሰቆቃ አይበልጥምና በግል የደረሱብኝን ነገሮች ሀዘኑንም እንደሀዘን ለማለፍ ፣ ሌሎች ምስቅልቅሎችንና በእኔና በቤተሰቦቼ ላይ የደረሱ ጊዜያዊ ስብራቶቼንም ለመጠገን የግድ የተወሰነ ጊዜ መውሰድ ስላለብኝ ፣ ከሚዲያውም ሆነ ከአንዳንድ የቀደሙ ተሳትፎዎቼ ለጥቂት ጊዜ መራቁ አማራጭ የሌለው ምርጫ ስለነበረ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የሚታዩ አሁናዊ ተገቢነት የሌላቸው ፣ መሪር ዋጋ የተከፈለበትን የህዝብ ትግል ጥቁር ጥላሸት በሚቀባ መልኩ እየተደረጉ ያሉ ጎራ ለይቶ (ከፋፍሎ) የመጠዛጠዝ ሁኔታ ፥ ልብ ሰባሪና ስሜትን የሚፈታተን በመሆኑ ፤ ከነመረጃ ክፍተቶቼ “ዘው!” ብዬ መግባት ባለመፈለጌና ሳላውቀው አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳርፍ ሀሳብ ላለማንሸራሸር ከመጠንቀቅም የመነጨ ነው።

በዚህ አጋጣሚ ገንቢነት የሌለው እኩይ አፍራሽ ሀሳብን ሀላፊነት በጎደለው መልኩ ከማንሸራሸር ''አወንታዊ ዝምታ'' ለህዝብ ውለታ ከመዋል እኩል ነውና አንዳንዶቻችን ራሳችንን ''ምን እያደረግን ነው?'' ብለን እንድንጠይቅም ለማስታወስ እወዳለሁ!

ከዚያ ባሻገር ግን ላንጨርሰው የጀመርነው ጉዞ ባለመኖሩ ፣ ልክ እንደትናንቱ በአንባገነኖች የሚደርስብንና እየደረሰብን ያለውን ግፍና መከራ በፅናት ተቋቁመን ፤ ይህን መሪር ዋጋ የተከፈለበትና እየተከፈለበት ያለውን የፍትህና የርትዕ ትግል ከግብ ለማድረስ በሚደረገው ሁሉን አቀፍ ትግል የድርሻችንን ለመወጣት ፣ ከሞት በስተቀር ወደኃላ የሚያስቀረን አንዳችም ምድራዊ ሀይል ሊኖር አይችልም! ከዚህ ውጭም ምርጫ የለምና!👍 ሠላማችሁ ይብዛ!

#ፍትህ በተለያዩ ወህኒ ቤቶች በግፍ ታግተው የመከራ ጊዜን እያሳለፉ ለሚገኙ ወንድም እህቶቻችን!


ቢመረንም እንዋጠው!

//Re-Posted //

አብዛኛው የአማራ የፖለቲካ ኤሊት ፥ እርስበርሱ የሚራኮተውና የማይግባባው ፥ አጋጣሚውን ጠብቆ ራሱን ለማንገስ ፥ ዘውዱን በጃኬቱ ኪስ ይዞ ስለሚዞር ነው! ሁሉም የሚፈልጉት መሪ መሆን ብቻ ነው፡፡

በመድረክ ድስኩር ሁሉም " የአማራ ህዝብ ከተደቀነበት የህልውና አደጋ ለመሻገር አንድ ሆኖ ተደራጅቶ መታገል አለበት!" ይሉህና እነርሱ ግን አንድ አይሆኑም፡፡ ስሜትና ፍላጎታቸውን አምቀው ስለህዝብ ሲሉ በአንድነት ቆመው ለጋራ ህዝባዊ አላማ አይታገሉም! ይህን ማድረግ የሞት ሞት መስሎ ይታያቸዋል፡፡

ለዚያም ነው " ስልጣን ለሰጣቸው ሁሉ" እንደህዳር አህያ የሚጫኑት!

በመሆኑም መሠረታዊ አጀንዳቸውን ጥለው እርስበርስ ሲራኮቱና ጠልፎ ለመጣጣል ሴራ ሲሾራረቡ ፥ ሠፊው የአማራ ህዝብ በእነሱ ጦስ የመከራ ቀንበሩን ተሸክሞ የመጣ የሄደውን ግፍ እያስተናገደ የግፍ ዘመን ሄዶ ሌላኛው የግፍ ዘመን ይተካል!

መደማመጥ ፥ መተባበርና መከባበር ያልቻለ ኤሊት ፥ ህዝብን አስተባብሮና አከባብሮ በአንድነት ሊያታግልም ሆነ ሊመራ አይችልም !

ምክንያቱም ህዝብን የሚፈጥረው ፈጣሪ ቢሆንም ፤ የህዝብን ማህበረሰባዊ ስነልቦና የሚቀርፀው ብሎም ፥ ውስጣዊ አንድነቱን በማጠንከር የትግል አቅጣጫዎቹን ፈር የሚያስይዘው የፖለቲካ ኤሊቱ ስለሆነ ነው!

ይህ ነጭ እውነታ ነው፡፡ ቢመረንም እንዋጠው፡፡ ራሳችንን ፈትሸን መከራ ስለሚዘንብበት ህዝብ ስንል ወደራሳችን እንመለስበት!👍


ያለምንም ምክንያት ከአንድ ዓመት ለሚበልጥ ጊዜ የታሠረው ወንድማችን ስንታየሁ ቸኮል ዛሬ አመሻሹን ከእስር ተፈቷል።

እንኳን ለቤትህ አበቃህ!

ሌሎች በግፍ ግዞት የሚሰቃዩ ወንድም እህቶቻችንንም በአስቸኳይ ፍቷቸው!


ከአንድ አመት መጠፋፋት በኃላ ይኸው ተመልሰናል!

አሳሪዎቼ እኔንና በዙሪያዬ ያሉ ሠዎችን ለጊዜው ማንገላታት ፣ ማበሳቆል አንዲሁም ህይወታችንን ማመሰቃቀል ተችሏቸው ሊሆን ይችላል። ነገርግን በፍፁም ሊሰብሩኝ አልቻሉም ፣ አይችሉምም!

አዎ! አ ል ተ ሰ በ ር ኩ ም! አልሠበርምም!

በእነዚያ አስቸጋሪ ጊዜያቶች ከጎኔ ለነበራችሁ ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ!

እውነት ያሸንፋል!👊


ተገቢና ለሌሎች አካባቢዎችም አርአያ የሚሆን መልእክት ነው!

👇👇👇

ከደብረታቦር ፋኖ - ለደ/ታቦር ከተማ ነዋሪዎች የተላለፈ መልእክት‼️

1.ማንኛውም የከተማው ነዋሪ በየሰፈሩ ጥይት የሚተኩስና አካባቢን የሚረብሽ አካል ላይ መሳሪያውን ከመውረስ ጀምሮ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ እንወስዳለን፡፡

2.ፋኖም ይሁን ሌላ ግለሰብ ሁኔታዎችን እንደአጋጣሚ ተጠቅሞ ፣ የመንግስት አመራር የነበሩ አካላትንና ሌሎችንም ሲሳደብ ፣ ሲያስፈራራ ፣ ሲያሸማቅቅና ተገቢ ያልሆኑ ተግባራትን ሲፈፅም ከተገኘ በተመሳሳይ መልኩ እርምጃ ይወሰድበታል።

3.የመንግስት ሰራተኛ የሆናችሁ ከቀን 27/11/2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደስራ ገበታችሁ እንድትመለሱ። ባንኮችና ሌሎች የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም በተመሳሳይ መልኩ መደበኛ የስራ እንቅስቃሴአችሁን ያለስጋት ማከናወን እንድትጀምሩ

4.የባጃጅ አገልግሎት እስከ በጌምድር ድረስ ባለው ቀጠና መደበኛ አገልግሎት መስጠት እንዲጀመር

5. በመንግስትም ሆነ በግል ተቋማት ላይ ''በፋኖ ስም'' ለመፈፀም የሚንቀሳቀስ ማንኛውንም ግለሰብ ላይ አስቸኳይና የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድበት ከወዲሁ በአንክሮ ለማስገንዘብ እንወዳለን!

//ሐምሌ 26/11/2015 ዓ.ም - ደብረታቦር //


ተስማምተው በህብረት ያበዱት ''መንግስት ነን'' የሚሉት አካላት ፦👇

ጧት ማታ የመከራና የችግር ድግስ ከመደገሳቸው በላይ ራሳቸው የፈጠሩትን ችግር ''እንፈታለን' ብለው የሚሄዱበትና ሌላ ተራራ የሚያህል ችግር የሚያበቅል መንገድ እጅግ ያናድደኛል!

ሰዎቹ የተለከፉት ምን አይነት አስከፊ ህመም እንደሆነ ከፈጣሪ ውጭ የሆነ ጠንቋይ ካልሆነ በስተቀር ለመረዳት ያዳግታል!

ሰው በዚህ ደረጃ እንዴት ይነቅዛል ? ይደነቁራል ? ይታወራል?

የራስን ንቅዘት እንኳ መለ'ስ ብሎ ለመፈተሽ የማያስችል ክፉ ቡድናዊ ህመም....!


መረጃ‼️

ደቡብ ወሎ_ደሴ

በትናንትናው እለት በከተማዋ በሚገኜው የ'ወሎ-ባሕል-አምባ' አዳራሽ አንድ ትልቅ ስብሰባ ተከናውኗል። ስብሰባው ከዞን ፣ እና ወረዳ ሚልሻ ጽ/ቤት ዘርፍ ኃላፊዎችን ያካተተ ሲሆን ፤ በክልሉ የሚሊሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ልጃለም ፣ በደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አሳመን ፣ እና በደሴ ከተማ ከቲባ ኃላፊ በሆኑት አቶ ሳሙኤል ጥምረት የተመራ ነበር።

ከአማራ ልዩ ኃይልነት ወደ መደበኛ ፓሊስነት የገቡ የቀድሞው የልዩ ኃይሉ አባላት ፣ እና በዞኑ ውስጥ ያሉ ወረዳዎችን የጸጥታ፣ እና ሚሊሻ ዘርፍ ቢሮዎችን በኃላፊነት የሚመሩ የብልጽግና ካድሬዎች ተሳታፊዎች የነበሩ ሲሆን ፤ የመድረኩ አላማም የልዩ ኃይል አባላቱን (ወደ ፖሊስነት የገቡ) በጥቅም በመደለል (አደራጅተን ቤት መስሪያ መሬት እንሰጣለን) እና በማሳመን ፤ ከየወረዳዎቹ ከሚገኙ ታጣቂ ሚሊሻዎች ጋር አቀናጂቶ በሰላም አስከባሪ ስም ወደ ወንድሞቻቼው (ፋኖ) መላክ ፣ እና እርስበርስ ማገዳደል ሲሆን ፤ መድረኩ ፍሪያማ ሳይሆን መቅረቱ ታውቋል።  በተለይ ከቀድሞዎቹ የአማራ ልዩ ኃይል አባላቱ በኩል፣ ያልተጠበቀ እና ከፍተኛ የሆነ ቅሬታ ተሰንዝሯል።

ብአዴን ልዩ ኃይሉን ከበተነ በኃላ ጭንቀት ውስጥ መግባቱ ግልጽ ሲሆን ፤ ይህንን ጭንቀቱን ለማቃለል "ሰላም አስከባሪ" የሚል ቡድን ለማዋቀር ወስኖ ወደ ስራ የገባ ሲሆን፤ በቅርቡ በክልል ም/ቤት ደረጃ የተወሰነ ሲሆን ፥ መዋቅሩም ከክልል እስከ ቀበሌ በየደረጃው የሚወርድ ሆኖ ፤ ያፈረሰውን የአማራ ልዩ ኃይልን ቦታ ተክቶ እንዲንቀሳቀስ የታለመለት ኃይል ሲሆን ፤ "የክልል ሰላም-አስከባሪ ዘርፍ" በመባል የሚጠራ መሆኑ ታውቋል።

//መረጃው ከምንጮቻችን እንደደረሰንን የቀረበ ነው።//


በድጋሜ የሚሰማኝን ለማጋራት ያህል ፦👇👇👇

በነፋስ ፍጥነት እየተጓዘ ያለውን ህዝባዊ ትግልና ቀጣይ ግቦችን ከህዝባችን ፍላጎት ጋር አሰናስኖ ለመጓዝ ፣ ትግሉ Urgent Strategic surgery and Leadership ይፈልጋል‼️

ባሻዬ! ከድል ዜናውና ከሙቀቱ ባሻገር ቅዝቃዜና በረዶ እንዳይከሰት እየተጠነቀቁና እያሰቡ መጓዝ ያስፈልጋል!

ከመነሻህ መድረሻህን ወስነህ መጓዝ ፣ ያለአንዳች ችግር ተጉዘህ በተገቢው ሰአት ላይ ከግብህ ለመድረስ ያስችልሃል!👍

መልካም ምሽት!


ማሳሰቢያ‼️

አንዳንድ በከፍተኛ ሙስና ውስጥ ተዘፍቀው ያሉ ካድሬዎች በምሽት ቢሮ ውስጥ ሰነድ በማቃጠል ''ፋኖ ነው ያረገው'' የሚል ጥላሸት ቀብተው ሰነድ በማጥፋት ፣ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ለመምታት እየሞከሩ መሆኑን ፣ ምንጮቻችን የቆቦ ማህበራት ሀላፊን ዋቢ አድርገው መረጃዎችን አድርሰውናል!

በመሆኑም ፦

ፋኖ ከህዝቡ ጋር ሆኖ የተቋማት ጥበቃና ደህንነትን ማረጋገጥ ብሎም ከተማ ውስጥ ያለን ወሮበላና አጋጣሚ ጠብቀው ለመዝረፍ ያሰፈሰፉ አንዳንድ ሀይሎች ላይ ከማስጠንቀቂያ ጀምሮ ተገቢውን የእርምት እርምጃ መውሰድ አለበት!


የአህያው ታሪክ..... !

//ለብአዴናዊነት የአስተሳሰብ ተሸካሚዎች በማዘኔ ምክንያት በድጋሜ የተለጠፈ//

….ከእለታት አንድ ቀን ንጉስ አንበሳ ቀበሮን ይጠራውና > ይለዋል። ቀበሮም ተደናግጦ ለአንበሳው ምግብ ፍለጋ ሲሄድ ከአህያ ጋር ይገናኛል፡፡

ይሄኔ አህያን የጦስ ዶሮ ለማድረግ የማታለያ ሀሳብ የመጣለት ቀበሮ ፥ > ብሎ በማሳመን አስከትሎት ይሄዳል፡፡

የተራበው አንበሳ አህያው ከአጠገቡ ሲደርስ ፥ ጊዜ ሳያጠፋ ተንደርድሮ ጆሮውን ግሽልጥ አድርጎ ይበላዋል፡፡ ይሄኔ አህያ ደሙን እያዘራ ሲሮጥ ከቀበሮ ጋር ይገናኛሉ፡፡

> ይለዋል፡፡

> ይልና አሳምኖ ይመልሰዋል፡፡

ድጋሜ አህያው ከአንበሳው ፊት ሲደርስ ተንደርድሮ ጭራውን ቆርጦ ይበላዋል፡፡ አሁንም አህያው ደሙን እያዘራ ሲሄድ ከደላላው ቀበሮ ጋር ይገናኛሉ፡፡

> ! >> ይለዋል፡፡

> ይልና በድጋሜ አሳምኖ ይወስደዋል፡፡

ይሄኔ አንበሳው አህያውን ደቋቁሶ ገደለው፡፡ ወደቀበሮውም ዘወር ብሎ > ሲል አዘዘው፡፡

ቀበሮ የታዘዘውን ፈፅሞ ለአንበሳው ይዞ ቀረበ፡፡ ነገርግን ይዞ ከመጣው ስጋ ውስጥ ጭንቅላቱን ስለበላው ሊገኝ አልቻለም፡፡ ይሄኔ አንበሳው በንዴት ጦፈ፡፡ > ሲልም አፈጠጠበት፡፡

ቀበሮም የዋዛ አልነበረም > ብሎ በብልሃት በማሳመን ራሱን ከሞት አዳነ ይባላል፡፡

የሠው ልጅም ህይወት ለአንድና ለሁለት ጊዜ ሲሳሳት እንዲታረም ከሰጠችው እድል መማር ካልቻለ ፥ ከውድቀቱ በኃላ የመማር እድሉ ጠባብና ከባድ ዋጋ የሚያስከፍል ሊሆን ይችላል!




የደብረ ማርቆስ ህዝብ አደባባይ ወጥቶ ፋኖን መደገፉ ያስበረገገው የደብረ ማርቆስ ብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ ፥ በካድሬ ግሩፕ ያስተላለፈውን የጭንቀት መልእክት እዩልኝማ!

ለካ! አይኖቻችን ሁሉም ቦታ እንዳሉ ለመረዳት ብልጠት ይጠይቃል!😂

Показано 20 последних публикаций.